በድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ፅ/ቤት በሚገኝበት ቅጥር ጊቢ ውስጥ በተከናወነው ስነስርአት ላይ ም/ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ተኝተዋል::
ለመከላከያ ሠራዊት ክብር በተሰጠበት መርሀግብር የብልፅግና ፓርቲ አመራሮች የአስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የተለያዩ ተቋማት ሠራተኞች እና ከአዲስ አበባ የመጡ የሀገራችን የኪነጥበብ ባለሞያዎች ተሳትፈዋል::
“ለሀገር መከላከያ ክብር እቆማለሁ” በሚል መሪ ቃል የ2 ደቂቃ ፕሮግራም እንዲኖር በኪነጥበብ ባለሙያዎች የተደረገውን ጥሪ በመቀበል አጋርነታቸውን አሳይተዋል፡፡
ሁሉም በያሉበት ለአንድ ደቂቃ ቀኝ እጃቸውን በግራ ደረታቸው ላይ አድርገው በመቆም ለሃገር መከላከያ ሠራዊት ያላቸውን ክብር ገልጸዋል፡፡
በተጨማሪም ለአንድ ደቂቃ ባሉበት ሆነው ባለማቋረጥ እያጨበጨቡ ለመከላከያ ሰራዊቱ ያላቸውን ክብርና አጋርነት አረጋግጠዋል፡፡
በመርሐ ግብሩ ህግን ለማስከበር ተሰማርቶ ድል እየተቀዳጀ ላለው ለኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት ክብር በመስጠት፣ በህዝብና መንግስት የተጣለባቸውን ግዳጅ ሲወጡ በጁንታው ቡድን ክህደት የተሰዉ የመከላከያ ሰራዊት አባላትም ተዘክረዋል::
“ለሀገር መከላከያ ክብር እቆማለሁ” በሚል መሪ ቃል የድሬዳዋ አስተዳደር ነዋሪዎች ባሉበት ቦታ በመቆም ለመከላከያ ሠራዊቱ ያላቸውን ክብር አረጋግጠዋል::


