16ቱ የፀረ-ፆታዊ ጥቃት ቀናት ንቅናቄ በተለያዩ ሁነቶች ለማክበር ዝግጅት መጠናቀቁ ተገለፀ::

    የዓመቱ ከህዳር 15 እስከ 30 16ቱ የፀረ-ፆታዊ ጥቃት ቀናት ንቅናቄ በተለያዩ ሁነቶች ለማክበር ዝግጅት መጠናቀቁ የሆነ እና በዓለማቀፍ ዘንድሮ ለ 29 ጊዜ በሀገራችን ኢትዮጲያ ለ 18 ጊዜ ” ፆታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶችን የማይታገስ ትውልድን በጋራ እንፍጠር! ” በሚል መሪ ቃል የሚከበረዊን የ16 ቀናት የፀረ-ፆታዊ ጥቃትን በዓል በድሬዳዋ አስተዳደር በተለያዩ ሁነቶች ለማክበር ዝግጅት መጠናቀቁ ዓለማቀፉን በተለያዩ ሁነቶች ለማክበር ዝግጅት መጠናቀቁ የድሬ ዳዋ አስተዳደር ሴቶች እና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ከሪማ አሊ ገለፁ፡፡
    የድሬ ዳዋ አስተዳደር ሴቶች እና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ከሪማ ዛሬ ዓለማቀፉን የ16ቱ ፀረ-ፆታዊ ጥቃት ቀናት አስመልክተዉ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጪያ በድሬደዋ አስተዳደር በከተማ እና በገጠር ቀበሌዎች በተለያዩ ሁነቶች ህብረተሰቡ ፆታዊ ጥቃት የሚያስከትለዉን ዘርፈ ብዙ ችግሮች በአግባቡ ተረድቶ በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ፆታዊ ጥቃቶችን እንዲከላከል ብሎም በሴቶች ላይ የሚፈፀም ፆታዊ ጥቃትን የማይቀበል ትዉልድ ለመፍጠር ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
    በአስተዳደሩ ፆታዊ ጥቃት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ መሆኑን የገለፁት ወ/ሮ ከሪማ የከሮና ቫይረስ በሽታ ከተከሰተ ወዲህ በአስተዳደሩ 3 ፆታዊ ጥቃት መመዝገቡን እና በአሁኑ ወቅት 61 % ላይ የሚገኘዉን ፆታዊ ጥቃት በሚቀጥሉት 10 አመታት ወደ 5 % ለማዉረድ ከሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል ፡፡