በአስተዳደሩ የመንግሰት ተቋማት የ1ኛ ሩብ አመት ሱፐርቪዥን አፈጻጸም መድረክ ተካሄደ

    የድሬዳዋ መንግስት ተቋማት የ1ኛ ሩብ አመት የማናጅመንትና የሰራተኞች መድረክ ግንኙነት አግባብ፣ የሪፖርት ዝግጅትና የፕሮጀክት አፈጻጸም ደረጃ ሱፐርቪዥን አፈጻጸም መድረክ ተካሂዷል።
    በቀረበው ሱፐርቪዥን መድረኩ ከከፍተኛ አመራር እስከ ጽ/ቤት ደረጃ ያሉ አመራሮች የተሳተፉ ሲሆን የተለያዩ ገንቢ አስተያየቶች ቀርበዋል።
    በቀጣይ የማናጅመንትና የመንግስት ሠራተኞች መድረክ የግንኙነት አግባብ በመመሪያው መሰረት በቃለጉባኤ በመደገፍ መተግበር እንዳለበት፣ የሚዘጋጁ እቅድና ሪፖርቶች በአግባቡ ተገምግመው የጋራ በማድረግ እና በፕሮጀክቶች አፈጻጸም የገቢ ማነስ በመኖሩ ለፕሮጀክቶቻችን መዘግየት ምክንያት በመሆኑ ጠንካራ ክትትልና ድጋፍ መደረግ እንዳለበት ተጠቁሟል።
    በመጨረሻም በቀጣይ የሚሰሩ ስራዎች ጠንካራ ክትትል በማድረግ የተገልጋይ እርካታን ለመፍጠር በባለቤትነትና በአንድነት ስሜት ስራዎችን በመምራት በቀጣይ ጠለቅ ያለ ሱፐርቪዥን እንደሚደረግ በማወቅ ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባ ተገልጿል።
    ምንጭ ድሬደዋ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ፌስቡክ ገጽ