በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር ክቡር ሬሚ ማሬሾ የተመራ የልዑካን ቡድን በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ጉብኝት አደረገ፡፡

    በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር ክቡር ሬሚ ማሬሾ የተመራ የልዑካን ቡድን በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በመገኘት ከአመራሩ ጋር የወደፊት የትብብር መስኮች ዙሪያ ላይ ውይይት ያደረጉ ሲሆን በዩኒቨርሲቲው ውስጥ የሚገኙትን የተለያዩ አገልግሎት መስጫ መሰረተ ልማቶችን ጎብኝተዋል፡፡ በኮቪድ 19 ምክንያት ተቋርጦ የነበረውን የፈረንሳይኛ ቋንቋ ትምህርትም ለማስጀመር ስምምነት ላይ የተደረሰ ሲሆን ዩኒቨርሲቲው ለሚያከናውናቸው ተግባራት በትብብር ለመስራት የሚቻልበት ሁኔታዎችን የሚያመቻቹ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
    ምንጭ ድሬደዋ ዩኒቨርስቲ