የሕወሓት ጁንታ አመራሮች የሚገኙበትን ለጠቆመ 10 ሚልዮን ብር ሽልማት ማዘጋጀቱን የመከላከያ ሠራዊት አስታወቀ

    የመከላከያ ሠራዊት መረጃ ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጄነራል አስራት ዴኔሮ ዛሬ ረፋድ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የጁንታው አመራሮችን በአጭር ጊዜ በቁጥጥር ስር ለማዋል የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ሽልማቱ መዘጋጀቱን አስታውቀዋል።
    በዚህም የመከላከያ ሠራዊት የህወሓት ጁንታ አመራሮች ያሉበትን ቦታ ለጠቆመ የ10 ሚሊዮን ብር ሽልማት እንደሚሰጥ አመልክተዋል።
    የሕወሓት ጁንታ አመራሮች የሚገኙበትን የሚያውቅ ማንኛውም ግለሰብ በአካባቢው ለሚያገኘው የመከላከያ ሠራዊት አባል በአካል በመቅረብ ማሳወቅ አልያም በመከላከያ ሠራዊት የስልክ ቁጥር በ011 1 248573 መጠቆም እንደሚቻልም ተገልጿል።