የአስተዳደሩ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ለቢሮው ሰራተኞች የማነቃቂያና አቅም ግንባታ ስልጠና ለሁለት ተከታታይ ቀናት በኒው ብሎሰም ሆቴል ተሰቷል፡፡
በስልጠናው ለስራ ያለን ተነሳሽነት ለመፍጠር የሚያስችሉ የአእምሮ ዝግጁነትና የስራ ቦታ ማህበራዊ ግንኙነት ሪብራንዲግና የሀብት ማስመዝገብ ጽንስ ሀሳብና አስፈላጊነት እንዲሁም የስራ ስነ ምግባርን በተመለከተ ለሁለት ተከታታይ ቀናት ለፈፃሚ ባለሙያዎች ግንዛቤ ተፈጥሯል፡፡
በስልጠናው ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የመረጃ ማፍራትና ማብቃት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሚካኤል እንዳለ እንደተናገሩት የኮሙዩኒኬሽን የሚዲያ ስራ የጋራ በመሆኑ ሰራተኛው ከዛለ የሥራ መንፈስ በመውጣት አቅማቸው እንዲገነባና የሥራ ተነሳሽነታቸው ለማምጣትና መልካም የቡድን መንፈስ ለመፍጠር ታስቦ የተዘጋጀ ስልጠና ነው ብለዋል፡፡
እንደ አቶ ሚካኤል ገለፃም በላቀ ጥራት ስራዎችን መከወንና የጋራ ሃሳቦችን ጠንካራ እንደሚሆኑ በማሣየት የኮሙዩኒኬሽን ስርዓቱን ማዘመን ለማስቻል እንዲህ አይነት ስልጠናዎች በቀጣይ በቢሮው የተለያዩ ጥናቶችን በማጥናት የፈጻሚውን ክፍተት በመለየት የአቅም መገንባትና የቡድን ስሜት በመፍጠር ለተሻለ አፈጻፀም የማነሣሣት ስራዎደች የይከናወናሉ ብለዋል፡፡
በስልጠናው የተሳተፉ የቢሮው ፈጻሚ ባለሙያዎችም በሰጡት አስተያየት እንደዚህ አይነት ስልጠናዎች ቀጣይነት ቢኖራቸው ጥሩ ነው በማለት በቀጣይ ጊዜያት የሚዘጋጁ ስልጠናዎች የማነቃቂያ ስልጠናዎደች ተከታታይነት ቢኖራቸው ጥሩ ነው ብለዋል፡፡


