ለ2013 አጠቃላይ ምርጫ የብልፅግና ፓርቲ እጩዎች ዝግጅት መመሪያ ዙሪያ ውይይት ተካሄደ::

    የድሬዳዋ የብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች
    በድ/ዳ አስተዳደር የብልፅግና ፓርቲ ወክለው ለፌደራል፣ ለከተማ አስተዳደርና ለቀበሌ ምክር ቤት አባልነት የሚወዳደሩ እጩዎች ቅድመ-ዝግጅት ማስፈፀሚያ እቅድ ዙሪያ ተወያይተዋል።
    በድሬዳዋ አስተዳደር ብሎም በአገር አቀፍ ለሚካሄደው 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ የብልፅግና ፓርቲ እጩዎች ዝግጅት መመሪያ ዙሪያ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች እና መምሪያ ኃላፊዎች እንዲሁም የወጣትና ሴቶች ሊግ አመራሮች በተገኙበት ውይይት ተካሂዷል።
    በቀጣይ በመመሪያው ዙሪያ እስከታች አደረጃጀት ውይይት ይደረግበታል ተብሎ ይጠበቃል።
    ምንጭ: የብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ