በኮሮና ምክናየት ተቀዛቅዞ የነበረው የንግድ ግብይት አሁን ላይ እየተሻሻለ መምጣቱን በቀበሌ 09 የሚገኙ ነጋዴች ገለጹ፡፡

    በአስተዳደራችን በርካታ የንግድ ተቋማት ከሚገኝባቸው ቀበሌዎች አንዱ የሆነው የቀበሌ 09 አስተዳደር ሲሆን በቀበሌው በርካታ ቁጥር ያላቸው የተለያዩ የንግድ ተቋማቶች ይገኛሉ፡፡ ታዲያ እነኝህ የንግድ ተቋማት በአለማችን ብሎም በአገራችን እና በአስተዳደሩ በተከሰተው የኮሮና ወረሽኝ ሳቢያ የንግድ እንቅስቃሴው ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ በመቀዛቀዙ የንግዱ ማህበረሰብ ለከፍተኛ ችግር ተጋልጦ መቆየቱን ያነጋገርናቸው ነጋዲዎች ተናግረዋል፡፡
    ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መንግስት በሽታውን ለመከላከል ባስቀመጠው መመሪያ በመጠቀም የንግድ እንቅስቃሴው ወደ ቀድሞ ቦታው እየተመለሰ ነው ሲሉ በቀበሌው የሚገኙ ነጋዲዎ ገልጸዋል፡፡
    ነጋዴዎቹ አያይዘው እንደገለጹት ምንም እንኳን ተቀዛቅዞ የነበረው የንግድ እንቅስቃሴ አሁን ላይ የተሻለ ቢሆንም ከውጪ የሚገቡ የምግብ ፍጆታ እጥረት የተነሣ የዋጋ ንረት አስከትሏል፡፡ በመጨረሻም አሁን ለይ በሽታውን ለመከላከል የተቀመጠውን መመሪያ በአግባቡ ከመተግበር አንጻር በሸማቹ እና በንግዱ ማህበረሰብ ዘንድ ከፍተኛ መዘናጋቶች እየታየ ሲሆን ይህም በቀጣይ ከፍተኛ ዋጋ ሊያስከትል ስለሚችል ህብረተሰቡ እና የሚመለከታቸው አካላት ትኩረት ሊሰጡት ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
    ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡