በቀበሌው ልዩ ስሙ ገንደገራዳ በተባለው አካባቢ ቀጠና ሁለት ሰፈር 1 እና 2 በአካባቢ ልማትና ህብረተሰብ ተሳትፎ ተለይተው
ሊሰሩ በታቀዱ ፕሮጀክት ላይ የመስክ ምልከታ ተደረገ፡፡
በቦታው ላይ የቀበሌው ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሀሰን ኢጌ እንዲሆም የኮሙኒኬሽን እና የአካባቢ ልማት ማስተባበሪያ ሀላፊ አቶ አብዱልአዚዝ አህመድ ጨምሮ የድሬደዋ አስተደዳደር ህብረተሰብ ተሳትፎ እና ልማት ኤጀንሴ ሀላፊ አቶ ጎንፋ ሞሲሳ በቦታው ላይ በመገኘት ውይይትም አካሄደዋል፡፡
የቀበሌው ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሀሰን በውይቱ ወቅት እንደተናገሩት ቀደም ሲል በእነኝህ መንደሮች ሊሰሩ የታቀዱት ፕሮጀክቶች 195ሜትር እና 100ሜትር ርዝማኔ ያለው የፍሳሽ ውሃ መውረጃ የዲሽ ስራ እንደነበር በማንሳት ይህ ደግሞ ከቦታው አቀማመጥ እና ጥበት አንጻር ለነዋሪው ከሚሰጠው ጥቅም ይልቅ ጉዳቱ ያመዝናል ብለዋል፡፡
ዋና ስራ አስፈጻሚው አያይዘው እንደገለጹት አሁን ላይ የአካባቢው ነዋሪ ፍላጎት የዲሽ ስራ አለመሆኑን እና የኮብልስቶን የመንገድ ንጣፍ እንደሆነ በተደጋጋሚ የሚያነሱት ጥያቂ በመሆኑ ቀደም ሲል ሊሰራ የታቀደው የፍሳሽ ማሶገጃ የዲሽ ስራ ፕሮጀክት ተቀይሮ የነዋሪውን ፍላጎት መሰረት በማድረግ የኮብልስቶን መንገድ ንጣፍ ስራው በአጭር ግዜ እንደሚጀመርም ተናግረዋል፡፡
በቀበሌው የኮሙኒኬሽን እና አካባቢ ልማት ማስተባበሪያ ሀላፊ አቶ አብዱልአዚዝ አህመድ በበኩላቸው ልማትን ልማት የሚያደርገው የህብረተሰቡን የልማት ፍላጎት ሟሟላት ሲችል ብቻ መሆኑን በወቅቱ የገለጹ ሲሆን በነዋሪው ጥያቄ መሰረት የኮብልስቶን ስራውን በአፋጣኝ በመጀመር የነዋሪውን የልማት ጥያቄ እንመልሳለን ብለዋል፡፡
በመጨረሻም የ ኤጀንሲው ሀላፊ አቶ ጎንፋ ሞሲሳ የነዋሪውን ጥያቄ በመረዳት በአጭር ግዜ ውስጥ ወደ ተግባር ስራ ለመግባት ከስምምነት ደርሰዋል፡፡


