የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የንግድ ቤቶች የኪራይ ተመን የወቅቱን የገበያ ሁኔታ ታሳቢ ያደረገ ሊሆን እንደሚገባ ተገለፀ::
በኪራይ ማሻሻያ ተመኑ ረቂቅ ላይ የደንበኞች ግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት ተካሂዷል በመድረኩ የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ድሬደዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ እውነቱ ወርቅነህ አሁን እየተሰራበት ያለው የንግድ ቤቶች የኪራይ ተመን ላለፉት በርካታ አስርት አመታት ማሻሻያ ሳይደረግበት እስካሁን መቆየቱን ጠቁመዋል። በመሆኑም ከገበያ ተወዳዳሪነት ከግብር ስረዓቱ እንዲሁም ከፍትሐዊነት አንፃር ክፍተት አንዳለበት ገልፀዋል።ከዚህ ባለፈ ኮርፖሬሽኑ እንደአንድ የመንግስት የልማት ድርጅት…


