በኪራይ ማሻሻያ ተመኑ ረቂቅ ላይ የደንበኞች ግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት ተካሂዷል
በመድረኩ የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ድሬደዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ እውነቱ ወርቅነህ አሁን እየተሰራበት ያለው የንግድ ቤቶች የኪራይ ተመን ላለፉት በርካታ አስርት አመታት ማሻሻያ ሳይደረግበት እስካሁን መቆየቱን ጠቁመዋል።
በመሆኑም ከገበያ ተወዳዳሪነት ከግብር ስረዓቱ እንዲሁም ከፍትሐዊነት አንፃር ክፍተት አንዳለበት ገልፀዋል።ከዚህ ባለፈ ኮርፖሬሽኑ እንደአንድ የመንግስት የልማት ድርጅት የተቋቋመበትን አላማ ለማሳካት ብሎም የተጣለበትን ኃላፊነት ለመወጣት የሚያስፈልገውን ገቢ ለመሰብሰብ እንዲቻለው የኪራይ ማሻሻያ ተመን ማስፈለጉን አቶ እውነቱ አስረድተዋል።
በውይይቱ የተሳተፉ ደንበኞች በኪራይ ማሻሻያ ተመኑ ረቂቅ ላይ በርካታ ጥያቄና አስተያየት አንስተው ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል።በአጠቃላይ የኪራይ ተመኑ የድሬደዋን ነባራዊ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ ሊሆን አንደሚገባ መግባባት ላይ ተደርሷል።


