ድሬዳዋ በመጀመሪያው የቴኒስ ውድድር ድል ቀናት።

    የኢትዮጵያ ቴኒስ የክልሎች ሻምፒዮና ውድድር ዛሬ በድምቀት ሲጀመር ድሬዳዋ ተጋጣሚያቸውን በማሸነፍ በድል ጀምሯል ፡፡
    # በዛሬው ዕለት በተካሄዱት የመክፈቻ ጨዋታዎች በወንዶች ድሬደዋ ከሐረሪ ሁለት የነጠላ አንድ የጥንድ ጨዋታ አድርገው ድሬዳዋ 2 ለ 1 በሆነ አጠቃላይ ውጤት አሸንፏል፡፡
    # በወንዶች አዲስአበባ ከደቡብ ሁለት የነጠላ አንድ የጥንድ ጨዋታ ያደረጉ ሲሆን አዲስ አበባ 3 ለ 0 አጠቃላይ ውጤት አሸናፊ ሆኗል ።
    # በሴቶች አማራ ከሀረሪ ሁለት የነጠላ አንድ የጥንድ ጨዋታ አድርገው ሐረሪ 3 ለ 0 በሆነ አጠቃላይ ውጤት አሸናፊ መሆን ሲችል ፤
    # በሴቶች አዲስ አበባ ከደቡብ ሀለት የነጠላ አካሂደው አዲስ አበባ 3 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።
    # ውድድሩ ከጥር 22 – የካቲት 02 /2013 ዓ.ም ለተከታታይ ቀናት የሚካሄድ ሲሆን ከአራት ክልሎችና ከሁለት ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ ወንድ 30 ሴት በድምሩ 60 ተወዳዳሪዋች ተሳታፊ ሆነዋል