መልዕክተ ድሬ 708

    የምርጫ መመዘኛ ነጥቦችን በጥቂቱ

    አዘገጋጅ፡ ስንታየው እንግዳ

    ህይወት በምርጫ የተሞላች ናት፡፡ ከፊት ለፊታችን የተሰደረው ሁሉ የሚረባን ነው ማለት አይቻለም ለዚህም ነው ከአንዱ ሌላውን ከሌላው ደግሞ ሌላ የተሻለውን ለመምረጥ ዙሪያችንን የምናማትረው አንዳንዴ ከትልቁ መጥፎ ትንሹን መጥፎ መምረጥ የሚባለው ምርጫ አንዱ የህይወታችን ክፍል ስለሆነም አይደል፡፡ ከምግብ መርጠን እንበላለን፣ ከልብስ መርጠን እንለብሳለን፣ ማህበራዊ ህይወታችን በጠቅላላ በምርጫ ዙሪያ የሚሽከረከር ነው ስናፈቅር እንኳን በዘፈቀደ ሳይሆን ልባችንን የሞላልንን እና ለዓይናችን ያማረንን እንመርጣለን፡፡

    እናም ከላይ እንደጻፍኩት  ህይወታችን በምርጫ የተሞላች ናት በጀማ የሚንቀሳቀሱ የዱር እንሰሳት ከሰማይ በራሪዎቹ እስከ በምድር ተንቀሳቃሾቹ አብዛኛዎቹ በጋራ የሚኖሩ ሲሆኑ እንደየ አናኗራቸው ዘይቤ የሚመሯቸው አውራዎች አሊያም የቡድን መሪዎች አሏቸው፡፡ ታዲያ እነዚህ የቡድኑ አመራሮች የመሪነት በትረ ስልጣኑን የሚጨብጡበት መንገድ አንድም ከቡድኑ ውስጥ  ጉልበተኛ የሆነ እንደሆን አሊያም ከአጥቂ ጠላት መንጋውን ማስመለጥ የመችልና አቅሙ በተለያዩ አጋጣሚዎች ተፈትኖ እራሱ መንጋው በራሱ ቋንቋ እና እንቅስቃሴ እውቅና ሲሰጠው እንደሆነ በተለያዩ እንሰሳት ዙሪያ የተለያዩ ጥናቶችን የሚያደርጉ አካላት ይናገራሉ፡፡ይህ የእንሰሳቱ ዓለም ህይወት ነው::…ይቀጥላል… ለበለጠ መረጃ ገፅ 5 ያንብቡ..መልዕክተ ድሬ 7 0 8

    ጂሚ…ጂሚ…ጂሚ…አቻ…አቻ…አቻ…

    አዘገጋጅ፡በአፈንዲ ሙተቂ

    እስቲ አሁን ደግሞ በትዝታ ሰረገላ እየበረርን ወደ ልጅነት ዘመናችን እንሂድ። “ሀደል በደል ደሜር ለጉመር”እንዲሉ የሶማሊ ወንድሞቻችን (“ነገር ቢበዛበአህያ አይጫንም” ማለታቸው ነው)። በምስሉ ላይያለውን ሰውዬ ታውቁታላችሁ አይደል?… አዎን! ህንዳዊ የሲኒማ አክተር ነው፡፡ በትክክለኛ ስሙ “ሚቱን
    ቻክራቦርቲ” ይባላል፡፡ የሀገራችን የሲኒማ አፍቃሪዎች ግን “Disco Dancer” በሚባለው ፊልም ውስጥ
    በሚጠራበት ስሙ ነው የሚጠሩት፡፡አዎን! “ጂሚ” ነው፡፡ ያ “እኔ የዲስኮ ዳንሰኛ ነኝ” እያለ
    የሚሞላቀቀው ጆሊ!! …ለበለጠ መረጃ ገፅ 7ያንብቡ መልዕክተ ድሬ 7 0 8

    የፍቅር ግፍ ልቦለድ…

    አዘገጋጅ፡ በቴዎድሮስ አሰፋ

    እቀናለሁ ቅናቴ ግን በአንድ ጉዳይ ብቻ ነው፤በፍቅርና በፍቅረኞች ላይ፡፡ ያው በጎ ቅናት ልትሉት
    ትችላላችሁ እናም እቀናለሁ ጓደኞቼ ከፍቅረኞቻቸው ጋር ተቃቅፈው እየተሳሳቁ ወክ ሲያደርጉ ሳይ፣ ካፌ
    ተቀምጠው ሲገባበዙ ሲጎራረሱ ሲሳሳሙ ሳይ እቀናለሁ፡፡ ‹‹መቼ ይሆን እኔም ከሰው እኩል
    የምሆነው?›› እላለሁ ከጓደኞቼ በታች የሆንኩ ያህል ይሰማኛል መቼ ይሆን እኔም ፍቅረኛ ኖሮኝ አንገቷን
    አቅፌ እጇን በወገቤ ዙሪያ ጠምጥማ ቀልድ እያወራሁላት እየተሳሳቅን ሽርሽር የምንለው እላለሁ፡፡ በተለይ የገና በዓል ሲደርስ ጓደኞቼ ለፍቅረኞቻቸው ስጦታ ገዝተው ሲሠጡ ሳይ
    እቀናለሁ፡፡ስልክ እየደወሉ ‹‹የኔ ፍቅር›› ‹‹የኔ ማር›› እንዴት
    እንደናፈቅሽኝ›› ሲባባሉ ስሠማ እቀናለሁ…ለበለጠ መረጃ ገፅ 8 ያንብቡ መልዕክተ ድሬ 7 0 8