የድሬዳዋ አስተዳደር ግብርና ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ አዲስ ለተቀጠሩት የልማት ጣቢያ ሰራተኞች ስልጠና ተሰጠ::

    በመንግስት ሰራተኞች የስራ ስነ-ምግባር ዙሪያ ግንዛቤ ለመፍጠር የተዘጋጀ ስልጠና ተሰጠ፡፡
    በስልጠናው ላይ በተለያዩ ቀበሌዎች የተመደቡ ሰራኞች ተሳትፈዋል፡፡
    በስልጠናው ላይ መክፈቻ ንግግር ያደረጉት አቶ ኤልያስ አሊዪ የድሬዳዋ አስተዳደር ግብርና ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ምክትል ሃላፊ አርሶ አደሩን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ እንዲጠቀሙ ማስቻል ይጠበቅባችኋልለለበሙያቹ ማህረሰቡን ማገዝ አለባችሁ፡፡በስራችሁ ውጠየት ማስመዝገብ ይኖርባችኋል ብለዋል፡፡
    በከፍተኛ የሃላፊነት ስሜት ልማትን ማፋጠን አለብን ሲሉ አክለዋል፡፡
    በእንስሳት ጤና፣እርባታ፣የሰብል ባለሞያነት የሚሰሩ ሰራተኞች ቅጥር አድርጓል፡፡ለምርትና ምርታማነት ማደግ ወሳኝ የሆነው የሰው ኃይልን አሟልቶ መገኘት ሲቻል ነው፡፡የድሬዳዋ አስተዳደር ግብርና ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ የሰው ሃብት ዳይሬክቶሬት በገጠር ቀበሌዎች ያልተሟሉ ክፍት ቦታዎችን የማሟላት እንቅስቃሴ ውስጥ ይገኛል፡፡
    ተገልጋዩ ሕብረተሰብ በመንግስት ሠራተኞች በሚሰጡ አገልግሎቶች ላይ እምነት እንዲኖረው ለማድረግ፣የልማት ጣቢያ ሠራተኞች የመንግሥትን ፖሊሲዎችን፣ ተልዕኮዎችንና ተግባራትን በውጤታማነትና በጥራት መፈፀም እንዲችሉ፣ አፈፃፀሙ ግልፅነትና ተጠያቂነት የሰፈነበት እንዲሆን ለማስቻል፤ብሎም የመንግስት ሰራተኞች የተጣለባቸውን ሀገራዊና ህዝባዊ አደራ በብቃት፣ በታማኝነት፣ በውጤታማነት ለመፈፀም በስነምግባር የታነፀ መሆን ስለሚገባ ስልጠናው ወደ ስራ በሚገቡበት ወቅት ወሳኝ ሚና እንደሚኒኖረው ታስቦ ተዘጋጅቷል፡፡
    ግብርና ኮሚኒኬሽን