ለሴት አካል ጉዳተኞች በስርአተ-ምግብ ዙሪያ የተግባር ተኮርና የክህሎት ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ::

    የድሬደዋ አስተዳደር የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳዮች ኤጀንሲ በአስተዳደሩ ለሚገኙ ለሴት አካል ጉዳተኞች በስነልቦናና የስርአተ ምግብ ዙሪያ የተግባር ተኮር ስልጠና ሰጥቷል፡፡
    የድሬደዋ አስተዳደር እንደ ሀገር የተቀመጠውን መቀንጨርን በ2030 ዓ.ም ዜሮ መድረስ ተግባርን ተቀብሎ ከመንግስት ተቋማት ከስራ ማስኪያጃ በጀት 2% በመቀነስ እቅዱን ለማሳካት እየሰራ ይገኛል ፡፡ ይህ በእንዲህ እነዳለም በአስተዳደሩ ያሉ 9 ሴክተሮች የተሰጧቸውን ተግባራት እየፈፀሙ ይገኛሉ ይህንንም ተከትሎ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ኤጀንሲ ለሴት አካል ጉዳተኞች በስርአተ ምግብ ዙሪያ የክህሎት ማበልጸጊያ ስልጠና ተሰጥቶአቸዋል፡፡
    የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ኤጀንሲ በዚህ ባዘጋጀው ስልጠና የኤጀንሲው የኃላፊ ተወካይ አቶ መሀመድ ኢብራሂም ባስተላለፉት መልዕክት እንደተናገሩት በአካባባያችን የሚገኙ ምግቦችን አመጣጥኖ በመመገብ አንድ ሰው በቀን ማግኘት ያለበትን አመጋገብ ስርአት በመከተል ጤናማ ዜጋ ለማምረት የተመጣጠነ የአመጋገብ ስርአቱን ይዘን መጓዝ ይኖርብናል ብለዋል፡፡
    የዜጎችን የማህበራዊ ደህንነትን ለማሻሻልና የተሻለ እድገት እንዲኖራቸው የተስተካከለ የስርአተ ምግብ በመመገብ የትውልድ ተሻጋሪ የሆነውን የመቀንጨርና የምግብ እጥረትን ለመከላከል በአስተዳደሩ ለሚገኙ የሴት አካል ጉዳተኞችን አጥቢ ሴቶች፤ እስከ 2 አመት ልጆች ያላቸውን እንዲሁም ለእናቶች ቅድሚያ በመስጠት ስልጠናው መዘጋጀቱን የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳዮች ኤጀንሲ የስርአተ ምግብ ተወካይ ወ/ሮ ረሄል ደነቀ ተናግረዋል