ህብረት ስራን ማጠናከርና መደገፍ ለአገራችን ብልጽግና መረጋገጥ መሰረት መሆኑ ተገለጸ

    በድሬዳዋ አስተዳደር ለከፍተኛ አመራሮች ስለ ህብረት ሥራ ማህበራት በማህበራዊና ኢኮኖሚ ጠቀሜታ በተዘጋጀው የንቅናቄ ማስጀመሪያ መድረክ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የግብርና ውሃ ማዕድን ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ በአስተዳደሩ የህብረት ስራ ልማት ውጤታማ ለማድረግ ሁሉም አመራሮችና ባለድርሻ አካላት በመተባበርና በመቀናጀት በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊና በፓለቲካዊ ያለውን ጠቀሜታዎች ያለውን ጠቀሜታ በመረዳት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ጠይቀዋል።
    የአስተዳደሩ ም/ከንቲባ አቶ አህመድ ቡህ የህብረት ስራ ማህበራት ንቅናቄ መድረክ በአስተዳደራችን ያሉ የስራ ኃላፊዎች በአስተዳደራችን የሚከናወኑ ማንኛውም የልማት ስራዎች ያለ ህብረት ስራ ማህበራት ምንም እንደሆኑ ተገንዝበው ዘርፉን በመደገፍ ያሉባቸውን መሰረታዊ ችግሮች በመፍታት በአንድነት መንቀሳቀስ ለላቀ ለውጥ እንድንተጋ የሚያስችል እንደሆነ እምነት የፀና ነው ብለዋል።
    ህብረት ስራን ሳንይዝ ሀገራችን የያዘችውን ፈጣን እድገት ማሳካት እንደማይቻል እና መሰረታዊ ችግርን ለመፍታትና ስኬትን ለማምጣት በህብረት መስራት ወሳኝ ነው ብለዋል የፌደራል የህብረት ስራ ኤጀንሲ ም/ዋ/ዳይሬክተር አቶ አብዲ ሙመድ።
    በመድረኩ የፌደራል ኤጀንሲው የዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ድሪባ በቀለ ስለማህበራት አጠቃላይ ሁኔታ አመጣጥ፣ አጀማመር፣ ጠቀሜታ፣ የሚታዩ ማነቆዎች እና በቀጣይ የሚጠበቁ ስራዎችን ዘርዝረው በገለጻ አቅርበዋል።
    በመጨረሻም ንቅናቄውን መሠረት በማድረግ የቀረበውን ሰነድ መነሻ በማድረግ ሰፊ ውይይት በማድረግ የእለቱ መድረክ ተጠናቀቀ።
    በንቅናቄው መድረክ የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች እና የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
    ምንጭ ድሬደዋ ብልፅግና ፓርቲ