የድሬዳዋ አስተዳደር ፍትህ ጸጥታ እና ህግ ጉዳዬች ቢሮ ሃላፊ አቶ ሙሳ ጠሃ የውይይት መድረኩን በከፈቱበት ወቅት እንደገለጹት በአስተዳደሩ የተጀመሩ የማህበረሰብ አቀፍ አደረጃጀት እና የሮንድ ስራዎች ጥሩ መሆናቸውን ገልጸው እየታዩ የሚገኙ ውስንነቶችን በመቅረፍ የማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት አሰጣጣችንን ስኬታማ ማድረግ ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡
በውይይት መድረኩ ላይ የማህበረሰብ አቀፍ የሮንድ ስራዎችን በተመለከተ ጽሁፍ ያቀረቡት የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አለሙ መግራ በበኩላቸው በአስተዳደር ደረጃ ጅምሮች ቢኖሩም ጠንካራ እና ደካማ ጎኖች ተለይተው ስራዎች መሰራት እንዳለባቸው የጠቀሱት ኮሚሽነር አለሙ የሌሎች ክልሎችን ተሞክሮ በመድረኩ እንደግብአት አቅርበዋል፡፡
የማህበረሰብ አቀፍ በምን አግባብ መደራጀት እንዳለባቸው የገለጹት የድሬዳዋ አሰሰተደዳር ፖሊስ ኮሚሽን የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ ዳሬክቶሬት ዳሬክተር ም/ኮ ትእግስት ተሸመ አሁን ያለውን አደረጃጀት በመከላስ በተጠናከረ መልኩ ስራዎች መሰራት እንዳለባቸው በውይይቱ ላይ ገልጸዋል፡፡
በውይይቱ መድረኩ ላይ የተለያዩ ሃሳቦች ከቤቱ ተነስተው ምክከር የተደረገበት ሲሆን በውይይት መድረኩ ማጠናቀቂያ ላይም ኮሚሽነር አለሙ የስራ መመሪያ ሰጥተዋል፡፡
በውይይቱ ላይ የሁሉም ከተማ እና ገጠር ፖሊስ ጣቢያ ሃላፊዎች የኮሚኒቲ ፖሊሲንግ ኦፊሰር አመራሮች እና የየቀበሌው የፀጥታ ሃላፊዎች ተሳታፊ ሆነውበታል፡፡
ምንጭ ድሬ ፖሊስ


