የጤና መድህን ያለውን ጠቀሜታ ህብረተሰባችን በሚገባዉ ልክ አዉቆ እንዲጠቀም ለማስቻል እነደሚሰሩ ገለፁ፡፡

    የኢትዮጵያ ጤና መድህን ኤጀንሲ ከድሬደዋ አስተዳደር ጤና መድህን ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ጋር በመተባበር ለሚድያና የኮሚኒኬሽን ባለሞያዎች የመህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህንን አሰመልከቶ በሀረር ከተማ በተሰጠው ስልጠና ላይ አስተያየት የሰጡ ተሳታፊዎች ከስልጠናው የጤና መድህን በርካታ ጠቀሜታዎች እንዳሉት ለመረዳት መቻላቸዉን ገልፀው ይህን ጠቀሜታዎች ህብረተሰባችን በሚገባዉ ልክ አዉቆ እንዲጠቀም ለማስቻል በሞያቸው ትኩረት ሰጥተው እነደሚሰሩ ገለፁ፡፡
    የጤና መድህን ምንነት ፣ የጤና መድህን በተለያዩ የዓለም ሀገራት አጠቃቀም እንዲሁም በሀገራችን የጤና መደህን ስርአት በኢትዮጰያ እና ከመገናኛ ብዙሀን ባለሞያዎች ምን ይጠበቃል? በሚሉ እርሶች ስልጠናው የተሰጠ ሲሆን ሰልጣኞች ከስልጠናው በኃላ የተለያዩ ጥያቄዎች አንስተው በኢትዮጰያ ጤና መድህን ኤጀንሲ የአባላት ምዝገባና መዋጮ ዳይሬከቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጉደታ አበበ እና በአቶ ዘመድኩን አበበ የኮሚኒኬሽንና ሞቢላይዜሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር መልስና ማብራሪያ ተሰጥቶበታል።
    በሀረሪ ክልል አምሰት ወረዳዎች እና በድሬደዋ አስተዳደር በዘንድሮ አመት የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን የተጀመረ ሲሆን ይህን መርሀ ግብር በክልሎቹ ለማስቀጠል በሚዲያ ባለሞያዋች አማካኝነት ተከታታይ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ መስራት አስፈላጊ መሆኑን ሰልጣኞቹ ገልፀው ለዚህም በትኩረት እንደሚሰሩ ገልፀዋል ፡፡