ድሬዳዋና የኢንደስቲሪን የትስስር ታሪክ ለመድገም በትኩረትና በቅንጅት ሊሰራ እንደሚገባ ተገለፀ ኢንደስቲሪዎችን ለማስፋፈፋት እና ዉጤታማነታቸውን ለማሳደግ ከድሬደዋ አስተዳደር እና ከምስራቅ ኢትዮጵያ አጎራባች ክልሎች ከተዉጣጡ የኢንደስቲሪ ባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ የካቲት 9 2013 ዓ.ም በድሬደዋ የውይይት መድረክ ተካሄደ፡፡

    ይህ የውይይት መድረክ የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ኤጀንሲ፣ የፌዴራል አነስተኛና መካከለኛ ኢንደስቲሪዎች ማስፋፊያ ባለስልጣን እና የኢትዮጰያ ሀገራቀፍ ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት በጋራ በተዘጋጀው ይህ መድረክ ላይ ንግግር ያደረጉት የድሬደዋ አስተዳደር ም/ቤት አፈ-ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ እንደገለፁት ድሬዳዋና ምስራቁ የሀገራችን ክፍል በቀደምት ጊዜያት ከኢንደስቲሪዎች ጋር የጠበቀ የትስስር ታሪክ እንደነበራቸው ገልፀዉ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ይህ ትስስራቸዉ ከታሪክ ዉጪ በተግባር እንደሌለ ጠቁመው የህን በመቀየር ድሬዳዋ ከኢንደስቲሪዎች ጋር የነበራትን የትስስር ታሪክ ለመመለስ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በትኩረትና በቅንጅት ሊሰራ የገባል ብለዋል ፡፡
    በዚህ የምስራቅ ኢትዮጵያ አጎራባች ክልሎች ኢንደስቲሪዎች ባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ ላይ ከድሬደዋ አስተዳደር ፣ ከሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፣ ከአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት፣ከሀረሪ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የተዉጣጡ የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ኤጀንሲ፣ የአነስተኛና መካከለኛ ኢንደስቲሪዎች ማስፋፊያ እና የዘርፉ ማህበራት ተወካዮች የተሳተፉበት በዚህ የምክክር መድረክ ላይ ቅንጅታዊ አሰራርን ይበልጥ በማጠናከር ኢንደስትሪዎችን ለማስፋፋት እና ዉጤታማነታቸዉን ለማሳደግ በጋራ ሊሰሩ በሚገቡ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አካሄደዋል፡