የድሬዳዋ አስተዳደር የብልፅግና ፓርቲ የምርጫ ምልክት የሆነውን የበራ አምፖል እና የፓርቲውን ማኒፌስቶ አበሰረ።

    የድሬዳዋ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መብራቴ ገብረየስ የእለቱን መድረክ መከፈቱን ባበሰሩበት ወቅት አምፖል ባለበት ብርሃን አለ ብርሃን ባለበት ተስፋ አለ ብለዋል።
    በመድረኩ የፓርቲውን ማኒፌስቶ እና የምርጫ መወዳደሪያ ምልክት የፓርቲው ኃላፊና የአስተዳደሩ ም/ከንቲባ አቶ ከዲር ጁሀር በጋራ በመሆን ይፋ አደረጉ፡፡
    አቶ ሮቤል ጌታቸው የፓርቲው የፖለቲካ አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ ምልክቱ በቀላሉ ማስታወስ የሚቻል፣ የተለየ፣ የፓርቲውን አላማ ያቀፈ እና ለትችት ያልተጋለጠ መሆን እንዳለበት አስተዋውቀዋል።
    የተዋወቀውን የበራ አምፖል ምልክትና ማኒፌስቶ በሶማልኛና በአፋን ኦሮሞ የአስተዳደሩ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ አብራርተዋል።
    በመጨረሻም ስለማኔፌስቶው አጠቃላይ ይዘት በፓርቲው ኃላፊ ቀርቦ በኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙር ተጠናቀቀ።
    ምንጭ:ድሬዳዋ ብልጽግና ጽ/ቤት