በድ /ዳ አስተዳደር በ 38 ገጠር ቀበሌዋች በትላንትናው እለት በይፋ የተጀመረው 8ኛው የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራ በላቀ የህብረተሰብ ተሳትፎ እየተከናወነ ይገኛል።

    በትላንትናው እለት በይፋ የተጀመረው 8ኛው የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራ ተሳታፊዎች እንደገለፁት የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት በዘላቂነት የሚከናወን የመስኖ ልማታችን ምሶሶ ፣ ለቀጣይነት ያለው ትውልድ ወደ ብልፅግና ለምናደርገው ጉዞ መሠረት የሚጥል ነው፣ እንዲሁም ባለፉት አመታት በተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራ የተገኙ መልካም ልምዶችን በማስፋትለላቀ ኢኮኖሚያው እድገት የማይተካ ሚና እንዳለው የተማርንበት በመሆኑና የህልውናችን መቅረት ነው በሚል ህብረተሰቡ በነቂስ ወጥቶ ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል።8ተኛው የተፋሰስ ልማት ስራዎች በትላንትናው ዕለት “የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ለሁለንተናዊ ብልፅግና” በሚል መሪ ቃል ተጀመረ።
    የድሬዳዋ ብልጽግና ፓርቲ አባላት እና የመንግስት ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በትላንትናው እለት በይፋ ተጀምሯል።