የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2013 ዓ/ም በተለያዩ የስልጠና ሙያ ያሰለጠናቸው ተማሪዎችን አስመረቀ፡፡

    የሀገራችን የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዘርፍ የሚመራበት የውጤት ተኮር ትምህርትና ስልጠና ስርዓት ከተዘረጋበት ጊዜ አንስቶ ዘርፉ የተጣለበትን ሀላፊነት በስራ ገበያው ፍላጎት ላይ የተሰመረተ በሞያ የበቃና በመልካም ስነ ምግባር የታነፀ መካከለኛና ዝቅተኛ ባለሙያ ለሀገሪቱ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት እንደሚወጣ ተገለጸ፡፡
    በዛሬው ዕለት የተመረቁት ተማሪዎች ከደረጃ 2 እስከ ደረጃ 4 በሰባት ዲፓርትመንት እንዲሁም 29 ተማሪዎች የሳተላይት ካምፓስ በ4 ዲፖርትመንቶች በመጀመሪያ ዲግሪ ያሰለጠናቸው በአጠቃላይ 1311 ተማሪዎች አስመርቀዋል፡፡
    በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ለተመራቂ ተማሪዎችና ቤተሰቦች የእንኳን ደስ አላቹ መልዕክት ያስተላለፉት የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ እንደተናገሩት የዘንድሮ ተመራቂ ተማሪዎችን ለየት የሚያደርገው በአለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተውን የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ የመማር ማስተማርና ስልጠና አሰጣጥ የተስተጓጓለ ቢሆንም ተማሪዎቹ የሚጠበቅባቸውን ኮርሶች ወሰደው በብቃት በማጠናቀቃቸው በዛሬው ዕለት ለምርቃት በቅተዋል ብለዋል፡፡
    የዕለቱ የክብር እንግዳ የነበሩት የአስተዳደሩ ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ ለተመራቂ ተማሪዎች ለኮሌጁ መምህራን እንዲሁም የተመራቂ ቤተሰቦችን እንኳን ደስ አላቹ ካሉ በኋላ ሀገራችን ከደህነት የምትወጣበትን የትምህርትና ስልጠና ዘርፎች ከምን ጊዜውም በላይ በማዘመን የኢንዱስትሪ ገበያው የሚፈልገው ብቃት ያለው የሰው ሃይል ማሰልጠን ትልቅ ድርሻ አለው ብለዋል፡፡
    በመጨረሻም በትምህርታቸው ጥሩ ውጤት ያመጡ ተማሪዎችና በዲፓርትመንቶች ጥሩ የሥራ ተሳትፎ ያደረጉ ተማሪዎች የሜዳሊያና ምስክር ወረቀት የተሰጠ ሲሆን ከኮሌጁ ጋርም የሥራ ግንኙነት የነበራቸው መንግስታዊና የግል ድርጅቶች የእውቅና ወረቀት ከዕለቱ ክብር እንግዳ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ እጅ ተረክበዋል፡፡