የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ በጤናው ዘርፍ በዩኒቨርስቲው ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ 19 ንድፈ ሀሳቦችን መርምሮ ለማፅደቅ ከባለድርሻ አካላት ጋር ለ2 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ግምገማ እየተካሄደ ነው፡፡
በዩኒቨርስቲው የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዲን አቶ በቀለ ያዜ በዛሬው ቀን እየተካሄደ ያለው ንድፍ ሃሰብ ግምገማ ቀደም ሲል የማህበረሰቡን የጤና ችግሮች ይቀርፋሉ ተብለው በህክምና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የታመነባቸው ንድፈ ሀሳቦች ላይ እየተወያዩ እንዳሉ ገልጸዋል፡፡
የማህበረሰቡን የጤና ችግር ሆነው ከማህበረሰቡ ጋር አብረው የሚኖሩ በሽታዎችን በመተፈሽ ጤናው የተጠበቀ ማህበረሰብ እንዲኖር ዪኒቨርስቲው በጀት መድቦ እየሰራ ነው ያሉት በህክምና ጤና ሳይንስ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት አስተባባሪ ረዳት ፕሮፌሰር አሊያ ኑሪ የተሰሩ ምርምሮች እታች ድረስ በማውረድ ችግር ፈቺ እንደሆኑም ታስቦበት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
ከ9 እስከ 14 ዓመት እድሜ ያሉ ሴት ህጻናቶች የማህጸን ጫፍ ካንሰር ክትባት አስመልክቶ የምርምር ንድፈ ሀሳብ ያቀረቡት መምህር ንጉሴ ካሴ እንደተናገሩት ሴት ህጻናቶች ክትባቱን እየተከተቡ ባለመሆናቸው ያለውን የጤና ችግር የዳሰሰ ጥናት ለማጥናትና የሚያስከትለውን ጉዳት የሚያሳይ ንድፈ ሀሳብ ይዘው መቅረባቸውን ገልጸዋል፡፡
መምህር ንጉሴ ከዚህም ጋር አያይዘው በሀገራችን በአንድ ዓመት ውስጥ 7 ሺህ ሰዎች እንደሚያዙና 5 ሺህ ሰዎች እንደሚሞቱ በማስገንዘብ በሽታው ምንም አይነት ምልክት ሳያሳይ ቫይረሱ 20-25 ዓመት ድረስ ሊቆይ በመቻሉ እድሜ በጨመረ ቁጥር በሽታው ሊከሰት ይችላል፡፡
ከዐይን ጋር ተያይዞ ያለውን የጤና ችግር ለማጥናት ንድፈ ሀሳብ ያቀረቡት መምህር ድልነሳ ፋንቴ እንደተናገሩት የዐይን ህመም በሽታዎች 80% መከላከል የሚችሉና በህክምና ክትትል የሚድኑ ናቸው በማለት ይህም በመሆኑ ለማህበረሰቡ ግንዛቤ ሊፈጠሩ የሚችሉ ጥናቶችን ለማጥናት ንድፈ ሀሳብ ማቅረባቸውን ገልፀዋል፡፡


