2.2 ሚሊዮን የኮቪድ 19 ክትባት የካቲት 28 ወደ ሀገራችን ኢትዮጲያ መግባቱ ይታወቃል ከዚህም ክትባት ውስጥ 6 ሺህ ለሚሆኑ ሰዎች መከተብ የሚያስችል ክትባት ወደ ከተማችን ድሬዳዋ መቷል ። ክትባቱ በነገው እለት በሀገር አቀፍ ደረጃ መሰጠት የሚጀምር ሲሆን በድሬዳዋ አስተዳደርም በነገው እለት በሳቢያን የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ክትባቱ የሚሰጥ ይሆናል።
ክትባቱ በሁለት ዙር መሰጠት እንደሚጀምርና የመጀመሪያ ዙር ክትባት ከተሰጠ በኋላ ከ 8 እስከ 12 ሳምንት ባለው ውስጥ ደግሞ ሁለተኛው ዙር ክትባት ቀድመው ለተከተቡ አካላት በድጋሚ እንደሚሰጥ የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ሀላፊ የሆኑት ወ\ሮ ለምለም በዛብህ ተናግረዋል ።
ወ\ሮ ለምለም በዛብህ አክለውም ክትባቱ በዋናነት የጤና ተቋም ላይ ላሉ ባለሞያዎች ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች እንደሚሰጥ ተናግረው በአሁን ሰአትም በከተማችን ድሬዳዋ ላይ የኮቪድ 19 ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ እየተሰራጨ ከመምጣቱም ባለፈ የማሟቾች ቁጥርም እየጨመረ እንደሚገኝና ነዋሪው ህብረተሰብም ከምን ጊዜውም በላይ የበሽታውን አስከፊነት ከግምት ውስጥ በማስገባት መጠንቀቅ እንዲገባቸውም ወ\ሮ ለምለም ተናግረዋል ።


