የድሬዳዋ አስተዳደር ቀበሌ 08 በተለምዶ ለገሃሬ የተገነባ ገበያ ማዕከል የሚገኙ 39 የማምረቻና መሸጫ ቤቶች ለተጠቃሚዎች በዕጣ መተላለፋቸውን ምክትል ከንቲባና የድሬደዋ ኢንዱስትሪ ክላስተር ልማት ኮርፖሬሽን የቦርድ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ከድር ጁሃር አስታወቁ፡፡
የንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አብዲ ሙክታር በበኩላቸዉ በድሬዳዋ አስተዳደር ከ 20ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ 6 ገበያ ማዕከላት ግንባታ ሲካሄድ እንደቆየ እና ከነዚህ ማዕከላት ሙሉ ለሙሉ ግንባታቸዉ ተጠናቀው የተረከብናቸውን ማዕከላት ለተጠቃሚዎቹ በማስተላለፍ የስራ አጥነትን ለመቀነስ ብሎም
በዕጣ አወጣጥ ሥነስርዓት ላይ ምክትል ከንቲባና የድሬደዋ ኢንዱስትሪ ክላስተር ልማት ኮርፖሬሽን የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ከድር ጁሃር ስለማምረቻና መሸጫ ቤቶቹ አስተዳደር ፤አያያዝና አጠቃቀም ሰፊ ማብራሪያና መመሪያ ሰጥተዋል፡፡
በዕጣ የተላለፉትም የማምረቻና መሸጫ ቤቶች አንድ በኮንስትራክሽን ዘርፍ ለተሰማራ፤አስራ አንድ በማኑፋክቸሪንግ ለተሰማሩ የቢሮና የቤት ዕቃ መሸጫና ቀሪዎቹ በሌሎች ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ለተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች በዕጣ ተከፋፍለዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት በአብዛኛው በአገራችን በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች እየተካሄደ ያለው መጠነ ሰፊ የልማት ስራ የሚያስፈልገው ለዘርፉ ልማት የሚያስፈልገው የሰው ሃይልም ሃገር ውስጥ ባሉ ተቋማት ደረጃ በሚሰጥ ስልጠና እና በአገር ውስጥ በሚገኝ ልምድ ሊከናወን የሚችል ነው፡፡
በተጨማሪም ኢንዱስትሪውን ለማሳደግ በመንግስት በኩል የተቀየሱ አመቺ ፖሊሲዎች በአገሪቱ የመኖራቸውን ሁኔታ በዘርፉ በከፍተኛ ደረጃ መጠቀም እንደሚቻል አመላካች ነው፡፡
እነዚህን ምቹ ሁኔታዎች ለመጠቀም አንድ ጥቃ/አነ/ኢንተርፕራይዝ ሁልጊዜም የትምህርት /ክህሎት/ የልምድ፣ የመሳሪያ እና የመስሪያ ቦታ አጠቃቀምና የስነ ልቦና ዝግጅት ሊኖረው ይገባል፡፡ መሰረታዊ አቅርቦቶችን አሟልቶ የሚገኝና በሂደት እያዳበራቸው ያለተቋቋመ ድርጅት ብቃቱ የተሟላ ነው ለማለት አይቻልም፡፡
በመጨረሻም በጥቂት አመታት ውስጥ የተገኙ አመርቂ ውጤቶች በዘላቂነት ለማስቀጠልና የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዳችንን ለማሳካት በዘርፉ በግንባር ቀደምነት የተሰማሩተቋማት እንደ ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት፣ ቴክኒክና ሙያ ቢሮና ብድርና ቁጠባ ተቋም የመሳሰሉት የድጋፍ ሰጭ ሚና ወሳኝነት አለው፡፡
ለስትራቴጂው ተፈፃሚነት ውጤታማነት አመራሩ አንቀሳቃሹ፣ ባለሙያው፣ የአንቀሳቃሽ ቤተሰቦች፣ ድጋፍ ሰጭ ተቋማት፣ ህብረተሰቡና የሚመለከታቸው አካላት ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ትኩረት ሰጥተው ሊረባረቡ ይገባል፡፡
ምክትል ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር ባስተላለፉት መልዕክት እነኝህን የማምረቻና መሸጫ ቤቶች ለሶስተኛ ወገን አሳልፎ ማከራየት እንደማይቻል ገልፀው ይህ ከሆነ በመመሪያዉ መሰረት የተቀመጡት ማስተካከያ እንደሚወስድ አብራርተዋል፡፡


