የ12ኛ ክፍል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ፈተና ባሳለፍናቸው 4 ቀናት በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተሰጠ እንደነበረ የሚታወስ ሲሆን ፈተናው እንደ አስተዳደራችን በስኬት መጠናቀቁን ነው ወ/ሮ ሙሉካ መሀመድ የተናገሩት፡፡
ወ/ሮ ሙሉካ አክለውም ፈተናው በስኬት እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ ሥራ ለሰሩት መምህራን፣ የፈተናው አስተባባሪዎች፣ ተፈታኝ ተማሪዎች እና የፀጥታ አካላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡
የዘንድሮ ተፈታኝ የሆኑ ተማሪዎችም በበኩላቸው ፈተናው እንደሚሰጥ በትምህርት ቤቶቻችን እንደተነገረን ከህዳር ወር ጀምሮ ስንዘጋጅበት ነበረ በፈተና ጊዜም ምንም ዓይነት ችግር አላጋጠመንም ብለዋል፡፡
ፈተናው በቅርብ ጊዜ እንደ ሀገር አቀፍ ውጤቱ እንደሚገለጽ ነው የተናገሩት ወ/ሮ ሙሉካ መሀመድ የአስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ፡፡


