የጠንካራ አንድነታችን ቀጣይነት
ለመጪው ትውልድ በማሰብ ይገለጣል
ለመጪው ትውልድ እንዳይተላለፉ ተማምለን የተነሳንባቸውን ሀገራዊ ጉዳዮች አሳክቶ እዳር የማድረሱ ኃላፊነት በዚህ ትውልድ ጫንቃ ላይ የወደቀ አደራነው፡፡ምክኒያቱም ያለፈው ትውልድ ከደም፣ከሥጋ፣ ከአጥንትና ከህይወት ውድ ዋጋ ከፍሎ ያቆያትን ይህችን መተኪያ የሌላት ሀገር በከበረና ትልቅ ዋጋ ሊሰጠው በሚገባ አደራያስረከበው ለአሁኑ ትውልድነው፡፡ ስለዚህ ይህም ትውልድ በተራው ለተረከበው አደራ ታማኝና ቁርጠኛ በመሆን መጪው ትውልድ እንዲኮራበት ሊያደርገው የሚችል ገድል ፈጽሞ ሊያልፍ ይገባል፡፡ ምክኒያቱም ሀገር ማለት ያለፈውም ያሁኑም የሚመጣውም ትውልድ ድምር ነውና፡፡
ለመጪው ትውልድ አይተላለፉም ብለን እጅ ለእጅ ተያይዘን ከተነሳንባቸው ጉዳዮች ዋና ዋናዎቹ አክራሪ ጽንፈኝነት፣የተራቆተ መሬት፣ድህነትና ኋላቀርነት፣ የኪራይ ሰብሳቢነትና የመልካም አስተዳደር ችግሮችና ሌሎችም ናቸው፡፡ እነዚህ ጉዳዮች መንግስትና ህዝብ የጋራ መግባባት የፈጠሩባቸው በመሆናቸው ሀገራዊ አጀንዳ ከመሆናቸው በተጨማሪ የሚበላንን ቦታ ብቻ እንከክ በሚለው ዘመን ተሸጋሪ አባባልና መመሪያ መሠረት ልዩ ትኩረት ተሰጥቷቸው ከፍተኛ ርብርብ ሲደረግባቸው ቆይቷል፡፡ እነዚህ አንገብጋቢ ጉዳዮች ላይ የተፈጠረውን ጠንካራ የጋራ መግባባት የበለጠ በማጠናከር በቀጣይም ልንረባረብባቸውይገባል፡፡ይቀጥላል…ለበለጠ መረጃ ገፅ 3 ያንብቡ መልዕክተ ድሬ7 1 3
ችላ ማለት ዋጋ እያሰከፈለን ነው!
መጀመርያ ላይ ከጥንቃቄ ብዛት ግርግር ተፈጥሮ ነበር፡፡ ቀስ በቀስ ግን እየለመድነው መደበኛ ነገር ሆነ፡፡ በኮሮና የተያዙ ሰዎች ቁጥር ጥቂት በነበሩበት ጊዜ ሰባት ሰዓት የጤና ሚኒስትር የዶክተር ሊያ ታደሰን ሪፖርት ለመስማት በጉጉት እንጠብቅ የነበረው አሁን በመቶዎቹ እና በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መያዝ ሲጀምሩ መስማት ትተናል፡፡ በአካባቢያችንም ቢሆን የኮሮና ቨይረስ ወደ ሀገራችን ከገባበት ቀን ጀምሮ ከመንግስት የሚሰጡ የተለያዩ መመርያዎችን በጥሩ ሁኔታሲተገበሩ ቆይተዋል፡፡ ለአብነትም የመንግስት ሠራተኞች በፈረቃ እንዲሰሩ ተደርጓል፡፡ የኮሮና መከላከያ ቁሳቁሶች ማለትም ሳኒታይዘር (አልኮል)፣ ሳሙና የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ማስክ በተለያዩ ጊዜያት ለማህበረስቡ በሚሰራበት መስርያ ቤት ተስጥቷል፡፡
ነገር ግን ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ግን በሀገራችን የሚሰተዋሉ መዘናጋቶች ዋጋ እንዳሰከፈሉን ቢታሰብበት ኪሳራው ሊቀንስ ይችላል ፡፡ ማለትም ሁሉም ሰው የራሱን ጥንቃቄ ቢያደርግ እራሰችንን እና ቤተስባችንን እንዲሁም ወዳጅ ዘመዶቻችንን ማትረፍ እንደምንችል ልብ ሊባል ይገባል፡፡ መዘናጋታችን የበለጠ ዋጋ ያሰከፍላል እንጂ ምህረት እንደማያመጣ ይታወቃል፡፡ የዛሬ መዘናጋት ለነገው ድቀት እንደሚሆን ሊታሰብበት ይገባል፡፡ መጠንቀቅ ከኮሮና ብቻሳይሆን ለሌላውም ነገር ጠንቃቃ ልንሆን ይገባል ፡፡ ማለትም ሳይቃጠል በቅጠል እንደሚባለው ማለትነው፡፡ ነገሮች እስከ ሚጎዱን እና ረጂ አካላት እስከ ሚያሰፈልገን ድረስ ዝንጉ መሆን ወይም ልቼኝነት አያዋጣንም፡፡ ሁሉን ነገር በጊዜ መላልና በጅለትይገባል፡፡ ካልሆነም ሲነግሩን ልንሰማ ግድ ይላል፡፡ በሌሎች ሀገራት ያየነውን ክስተት በኛም ሀገር አሰደንግጦናል ግን አንደነሱ እስከ ምንሆን መጠበቅ ሳይሆን መጠንቀቅ የበለጠ ይጠበቅብናል ፡፡ ለመጠንቀቅ ደግሞ የሞት ዜና መጠበቅ የለብንም፡፡ ይቀጥላል …ለበለጠ መረጃ ገፅ 10 ያንብቡ መልዕክተ ድሬ7 1 3
የተፋሰስ ልማት ስራን በአግባቡ በመስራት ሁለንተናዊ ብልጽግናችንን እናረጋግጣለን ሲሉ የገንደ ገበሬ አርሶ አደሮች ተናገሩ፡፡
ገንደገበሬ በአሰሊሶ ክላስተር ስር ከሚገኙ 9 የገጠር ቀበሌዎች ውስጥ አንዱነው፡፡ ቀበሌው በዋናነት በመስኖ ልማት ስራ የሚታወቅ ሲሆን በዚህም የቀበሌው አርሶ አደሮች የተለያዩ አትክልትና ፍራፍሬዎችን በማምረት ለገበያ የሚያቀርቡ ከመሆኑም በላይ የድሬዳዋ መገለጫም ጭምር የሆኑት አምቦሾክ፣ ቲምር እና ሌሎችም ፍራፍሬዎች የሚመረቱበት ቀበሌነው፡፡
የቀበሌው አርሶ አደሮች በመስኖ ልማት ስራቸው ውጤታማነት መሰረት የሆነውን የምንጭ ውሃ ለማጎልበት 8ኛው የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራ ላይ የተለያዩየ አፈርና ውሃ ጥበቃና እንክብካቤ ስራዎችን በከፍተኛ መነቃቃትና ተነሳሽነት እየሰሩይገኛሉ፡፡ በገንደ ገበሬ ገጠር ቀበሌ የግብርና ልማት ሰራተኛ የሆኑት አቶ ቦጋለ አባይነህ እንደገለጹት በዘንድሮው የተፋሰስ ልማት ስራ በቀበሌው 3.5 ኪ.ሜ የውሃ መሄጃ ካናል ጥገና፣ 2 ምንጮችን የማጎልበት ስራ፣ 1 ኪ.ሜ ጋራ ላይ እርከን፣ 1 ኪ.ሜ የመንገድ ጥገና እና 150ሜ/ኪ የኩሬ ጥገና ለመስራት ታቅዶ ወደ ተግባር መገባቱንና እስካሁን ባለው አፈጻጸም ደግሞ አራቱ እቅዶች ሙሉ በሙሉ መጠናቀቃቸውን እና የኩሬ ጥገና ስራው ብቻ ታቅዶ ከነበረው 150ሜ/ኪ 1000ሜ/ኪ የሆነው መጠናቀቁን ተናግረዋል፡፡ በአጠቃላይ ከእቅዱ አንጻር 90% የሚሆነውን ስራ ማጠናቀቃቸውን የሚገልጹት አቶ ቦጋለ ይህም ሊሆን የቻለው ቀበሌው አርሶ አደሮች የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራ በመስራታቸው ከማንም በላይ የሚጠቀሙት እራሳቸው መሆናቸውን በአግባቡ በመረዳታቸውና ከልባቸው በመስራታቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ይቀጥላል…ለበለጠ መረጃ ገፅ 1 ያንብቡ መልዕክተ ድሬ7 1 3


