በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ፖሊሲ፣ ስትራቴጂና ፕሮግራሞች ዙሪያ የዩኒቨርሲቲው መካከለኛ አመራርና መምህራን የ10 ዓመት እቅድ እና ቁልፍ ውጤቶች ላይ የስልጠናና የዉይይት መድረክ በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

    በሀገር አቀፍ ደረጃ በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የተዘጋጀውን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በአዲስ መልክ ስለተዘጋጀው የ10 ዓመት ፖሊሲና ስተራቴጂክ እቅድ ላይ የጠራ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ያለመ የስልጠናዊ ውይይት መድረክ ላይ የዩኒቨርሲቲው መካከለኛ አመራርና መምህራን ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
    ለሁለት ቀን የሚቆየው ይህኑ ስልጠናዊ ውይይት የመጀመሪያ ዙር መድረክ በንግግር የከፈቱት የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ኡባህ አደም ዩኒቨርሲቲው የተጣለበትን አገራዊ ተልዕኮ ለማሳካት በዩንቨርሲቲው በየደረጃ የሚገኙ አመራሮች ፣ መምህራን እና በአጠቃላይ የዩንቨርሲቲው ማህበረሰብ በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ያዘጋጀውን የ10 ዓመት ፖሊሲና ስተራቴጂክ እቅድ ላይ የጠራ ግንዛቤ ሊኖራቸው እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
    ዶ/ር ኡባህ አደም አክሎም ከመጋቢት 09 እስከ መጋቢት 10 /2013 ዓ.ም ድረስ ለሁለት ቀን የሚቆየውን የመጀመሪያ ዙር የስልጠናዊ ውይይት በአሁን ጊዜ ተግባራዊ እየተደረገ ባለው ፖሊሲና ስትራቴጂ ላይ ተደጋግመው ሲነሱ የነበሩ ክፍተቶችን ለመቅረፍ የላቀ ሚና እንደሚኖረው ጠቅሰው ተሳታፊዎች በጥያቄና በአስተያየት መልክ የሚሰጡትን ግብአቶችን በመውሰድ እና በማዳበር የተሻለና ውጤታማ ፖሊሲና ስትራቴጂ ለመቅረጽ የላቀ ሚና ይኖረዋል ብለዋል ፡፡
    በስልጠናው ላይ የከፍተኛ ትምህርት ንዑስ ዘርፍ ፖሊስና ስትራቴጂ ሰነድን ያቀረቡት የዩንቨርሲቲው አካዳሚክ ጉዳዩች ምክትል ፕሬዘዳንት ዶ/ር መገርሳ ቃሲም በበኩላቸው ከዚህ በፊት ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ ተማሪዎች ከተመረቁ በኋላ የሚያመጡት ውጤት ከፍተኛ የሆነ ችግር ነበረበት እንዲሁም በፖሊሲዎቹ ላይም ብዙ መስተካከል የሚገባቸው ጉዳዮችን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በመስተካከል ላይ እንደሚገኝ አብራረተዋል፡፡
    የስልጠናው መርሃግብር በሁለት ዙር ተከፍሎ የሚሰጥ ሲሆን በመጀመሪያ ዙር የዩኒቨርሲቲው መካከለኛ አመራር አባላትና ለመምህራን የሚሰጥ ሲሆን ከመጋቢት 13 -14 ቀን 2013 ዓ/ም ለዩኒቨርሲቲው የአስተዳደር ሰራተኞች ስልጠናው እንደሚሰጥ ታውቀዋል።