የመንግሥት አገልግሎት ዘርፍ የለውጥ ፍኖተ-ካርታና ፕሮግራሞች ላይ ሲሰጥ የቆየው የግንዛቤ ማዳበሪያ ተጠናቀቀ::

    ለድሬደዋ አስተዳደር ከመንግሥት ሠራተኞች የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥን ዘመናዊና ሳይንሳዊ ለማድረግ የመንግሥት አገልግሎት ዘርፍ ነፃ፣ ገለልተኛና ብቃት ያለው አድርጎ ለማደራጀት በተዘጋጀው የለውጥ ፍኖተ-ካርታ የሰው ኃብት ልማትና ብቃት ማረጋገጫ ማዕቀፍ፣ የመንግሥት አገልግሎት ዕሴት ግንባታና ሥነ-ምግባር እንዲሁም ጥራት ያለው የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥ ስርአት በሚሉ ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጎ በሀረር ከተማ ለሁለት ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የቆየው የግንዛቤ ማዳበሪያ ተጠናቀቀ፡፡
    በዚህ የግንዛቤ ማዳበሪያ ላይ ከድሬደዋ አስተዳደር የመንግስት መስሪያ ቤቶች ለተውጣጡ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሮች ፣ የሰው ሀብት ልማትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ኃላፊዎች፣የለውጥና መልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ኃላፊዎች፣ የስነ-ምግባር መኮንኖች፣ የቡድን መሪዎች እንዲሁም ለከፍተኛ ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን የለውጥ ፍኖተ-ካርታ አራት ትልልቅ ፕሮግራሞች ማለትም የመጀመሪያ ነፃ፣ ገለልተኛና ብቃት ያለው ሲቪል ሰርቪስ ግንባታ ሁለተኛ የሰው ሀብት ልማትና አስተዳደር ሥርዓት ሶስተኛው የእሴት ግንባታና ሥነ ምግባር እንዲሁም አራተኛው ውጤታማ የመንግሥት አገልግሎት ሥርዓት ግንባታ በሚሉ ፕሮግራሞች ላይ የግንዛቤ ማዳበሪያው ተሰጥቶዋል፡፡
    የስልጠናው ዓላማ የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥን ዘመናዊና ሳይንሳዊ በማድረግ የመንግሥት አገልግሎት ዘርፍ ውጤታማነትን በማሳደግ ዘርፉ ለሀገራችን እድገት የበኩሉን ድርሻ ማበርከት የሚችል ማድረግ የሚቺል በሁሉም የሲቪል ሰርቪስ ተቋማት፣ ነፃ፣ ገለልተኛና ብቃት ያለው አድርጎ ለማደራጀት በሀገራቀፍ ደረጃ በተቀርፀው የመንግሥት አገልግሎት ዘርፍ የለውጥ ፍኖተ-ካርታ ለመተግበር እንዲቻል ግንዛቤ ለመፍጠር ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን በመክፈቺያ ንግግር በፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ተስፋዬ በላቸው እና የአስተዳዳሩ ምክትል ከንቲባ አቶ አህመድ ቡህ አብራርተዋል፡፡