የኮንትሮባንድና ህገ-ወጥ ንግድ የሚያደርሱትን ዘርፈ-ብዙ ጉዳቶች ለመከላከልና ለመቆጣጠር በድሬዳዋ አስተዳደር የሚገኙ የፍትህ እና ፀጥታ አካላት እዲሁም የከተማ ቀበሌ ተወካዮች ጋር የኮንትሮባንድና ህገወጥ ንግድ በግለሰብ ፣ በህብረተሰብ ብሎም በሀገር ፓለቲካዊና ማህበራዊ ጉዳቶች ለመከላከል በሚቻልበት ሁኔታ ዙሪያ ውይይት ተካሄደ፡፡ በዚህ ውይይት ላይ የመክፈቺያ ንግግር ያደረጉት ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ኮንትሮባንድ በዘርፈ ብዙ መንገድ ማህበረሰብን የሚጎዳ፤ ለሀገር አለመረጋጋት መንስኤ ነው ያሉት ኮሚሽነሩ ውይይቱ የኮንትሮባንድን ጉዳት ለማስገንዘብ የንቅናቄ መድረኮች በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች እንደሚካሄዱ ጠቁመዋል፡፡ የኢንተለጀንስና ኮንትሮባንድ መከላከል ዳይሬክተር አቶ ተገኔ ደረሰ ፓለቲካዊና ማህበራዊ ጉዳቶችን በማድረስ ለግጭት መንስኤ በመሆን የአገር ደህንነትን አደጋ ላይ የሚጥል በመሆኑ ችግሩን የሚያባብሱ ሁኔታዎችን በመቆጣጠር ሁሉም ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ እንዲሆኑ ጠይቀዋል፡፡ በዚህ ውይይት ላይ በድሬዳዋ አስተዳደር የሚገኙ የፍትህ አካላት የቀበሌ እና የባለድረሻ አካላት ተወካዮች የሀይማኖት እና የሀገር ሽማግሌዎች የተሳተፉበት የንቅናቄ እና የዉይይት መድረክ ተካሄደ፡፡
በኮንትሮባንድና ህገ-ወጥ ንግድ የሚያደርሱትን ዘርፈ-ብዙ ጉዳቶች ለመከላከልና ለመቆጣጠር ህዝባዊ ንቅናቄ ተካሄደ ::


