በ ድሬ ደዋ አስተዳደር 38 ገጠር ቀበሌዎች ሲከናወን ለቆየው የ8ኛ ዙር “የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ለሁለንተናዊ ብልፅግናችን” በሚል መሪቃል በተፋሰስ ልማት ለተሳተፉ 76 የልማት ጀግኖች የዕዉቅና እና ሽልማት ተሰጠ፡፡
በዚህ የምስጋናና የእውቅና ስነስርዓት ላይ የግብርና ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ሀላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ እንደገለፁት በዘንድሮው የአርሶና የአርብቶ አደራችን የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃና እንክብካቤ ስራዎች በ38 ገጠር ቀበሌዎች በተከናወነ የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት 768 ሄክታር መሬት ላይ የተለያዩ የአፈርና ውሀ ጥበቃ ሥራዎችን በማከናወን 27,303,920. 00 ብር የሚገመት ተግባራት ማከናወን ተችሏል በዘንድሮውን የአርሶና የአርብቶ አደራችን የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃና እንክብካቤ ስራዎች የህልውና ጉዳይ እንደሆነ ባለፉት ዓመታት በተስሩ ስራዎች የጎለበቱ ምንጮች ማሳያ ናቸው።
የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት በተግባራት አፈፃፀም ወቅት ከጎናችን በመሆን ድጋፋቹን ለሰጣቹን የሁሉም ቀበሌ ነዋሪዎች ፣ የልማት አጋሮቻችን እንዲሁም በየደረጃው ለምትገኙ የአመራር አካላትና ባለሙያዎች ለነበራቸው ተሳትፎ ና ላበረከቱት አስተዋጽኦ እውቅና እና ምስጋና አቅርበዋል። የአፈርና ውሀ ጥበቃ ስራዎች ጥገና ፣የተሻሻለ የችግኝ ጉድጓድ ፣ማሳ ውስጥ የሚሰሩ ፣የማሳ እርከን ጥገና ፣የጎርፍ መቀልበሻ ቦይ ፣ፍግ ወደ ማሳ ማጓጓዝ እና በቀራ ነቀላ ከአብይ ስራዎች መካከል ናቸው::


