በዘንድሮው የ8ኛ ዙር የተፋሰስ ልማት በደማቅ ሁኔታ የመዝጊያ ስነስርዓት ተካሄደ
በድሬ ደዋ አስተዳደር 38 የገጠር ቀበሌዎች “የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ለሁለንተናዊ ብልፅግናችን” በሚል መሪ ቃል የአፈርና ውሀ ጥበቃ ስራዎች ጥገና ፣የተሻሻለ የችግኝ ጉድጓድ ፣ማሳ ውስጥ የሚሰሩ ፣የማሳ እርከን ጥገና ፣የጎርፍ መቀልበሻ ቦይ ፣ፍግ ወደ ማሳ ማጓጓዝ እና በቀራ ነቀላ ትኩረት አድረጎ ሲሰራ የቆዉ የተፋሰስ ልማት ስራ የመዝጊያ ስነስርዓት ላይ የክብር እንግዳ ሆነው ተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ተወካይ እና የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ ሱልጣን አሊዪ ባደረጉት ንግግር እንደገለፁት የገጠር ልማት ለከተማ ልማት መሰረት በመሆኑ በተለይም በገጠር የመጠጥ ውሃ አቅርቦት እና የመስኖ ማስፋፋት ስራዎችን አስተዳዳሩ በትኩረት እየሰራበት መሆኑን አብራርተዋል፡፡
የአርሶና የአርብቶ አደራችን ባለፉት ዓመታት በተስሩ የተፋሰስ ልማት ስራዎች ያመጡት ውጤት ይህ ስራ የህልውና ጉዳይ መሆኑን በመረዳቱ በዘንድሮዉ የተፋሰስ ልማት ስራ ስኬት ከፍተኛ አስተዋፆ ማበርከቱ ገልፀዋል፡፡
በስነስርዓት ላይ ለአራቱ የገጠር ክላስተሮች የዋንጫ እና ሰርተፊኬት የተበረከተ ሲሆን ለግብርና ልማት ጣቢያ ባለሞያዎች፣ለገጠር ቀበሌ ደጋፊ አመራሮች እንዲሁም ለገጠር ቀበሌዎች እንደ አፈፃፀማቸው ባለ ወርቅ እና ባለ ብር ደረጃ ሰርተፊኬት ተበርክቶላቸዋለ፡፡
በዚህ የ8ኛ ዙር የተፋሰስ ልማት ስራ ማጠቃለያ ላይ የገጠር ቀበሌዎች ሊቀመንበሮች ፣ የግብርና ባለሞያዎች የመንግስት እና የድርጅት ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በደማቅ የመዝጊያ ስነስርዓት ተጠናቋል፡፡


