በድሬ ደዋ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

    በዚህ ቅስቀሳ ስነስርዓት ላይ የብልፅግና ፓርቲ አባል የመንግስት ሰራተኞች የድጋፍ እና የቅስቀሳ ስነስርአት በከተማዋ የተለያዩ አቅጣጫዎች አካሄደዋል፡፡
    በቅስቀሳው ላይ የድሬደዋ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ መብራቴ ገብረየስ ፓርቲው በድሬ ደዋ እድገት ላይ እንቅፋት የሆነውን ቻርተር ማሻሻል፣ በከተማው ከአማርኛ ቋንቋ በተጨማሪ የአፋን ኦሮሞ እና ሶማሊኛ ቋንቋ የስራ ቋንቋ ለማድረግ በትኩረት እንደሚሰሩ ተናግረዋል ፡፡