በነገው ዕለት በአስተዳደራችን የሚጀመረውን የኢትዮጵያ ቤት ኪንግ ፕሪሚየር ሊግ እና በወቅታዊ ጉዳዮችን ዙሪያ ከመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የተሰጠ መግለጫ፡፡
በድሬዳዋ አስተዳደር አስተናጋጅነት የሚካሄደው 4ኛ ዙር የቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጫዋታዎች ከነገ መጋቢት 29/2013ዓ/ም ጀምሮ ለ5 ተከታታይ ሳምንታት ይካሄዳል፡፡ ይህንን እና ሌሎች ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የአስተዳደሩ መንግስት ኮሙዩኒኩሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ እስቅያስ ታፈሰ ለጋዜጠኞች ጋዜጣዊ መግለጫ ሰተዋል፡፡ በድሬዳዋ አስተናጋጅነት የሚካሄደው የኢትዮጵያ ቤት ኪንግ ፕሪሚየር ሊግ ለማዘጋጀትና ጨዋታን በስኬት እንዲጠናቀቅ አስፈላጊው ዝግጅት መጠናቀቁን የአስተዳደሩ…


