የደቻቱ ወንዝ ለልማት በማዋል ድሬዳዋን ማልማት ይኖርብናል።

    የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፈጡም ሙስጠፉ።
    ስድስት ሚሊዮን ብር በሚጠጋ ወጪ የደቻቱ ደረቅ አሸዋ ወንዝ ተፋሰስ የተቀናጀ የአየር ንብረት ለውጥ ማጣጣሚያ ኢኒቬቲቭ የፕሮጀክት ጥናት እየተደረገ ይገኛል፡፡
    የፕሮጀክቱ የቤዝ ላይንና የዲዛይ ጥናት ለድሬዳዋ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮችና በየደረጃው ለሚገኙ ባለድርሻ አካላት የማስተዋወቂያ መድረክ ላይ ንግግር ያደረጉት የአስተዳደሩ አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ እንደተናገሩት የደቻቱ ወንዝ ለልማት በማዋል ድሬዳዋን ማልማት ይገባል በማለት ከአሁን በፊት በደሬዳዋ የነበረውን አደገኛ ገጽታ ከጎርፍ የማዳኑ እና የቱሪስት መስህብም እንዲሆን እንዲሁም የስራ እድል ፈጠራ፤ ለወጣቶቹ ለመዝናኛ ቦታና ድሬዳዋ የምትታወቅበት የስፖርት መስህቦች መስራት የሚያስችል ይሆናል ብለዋል፡፡
    የድሬዳዋ አስተዳደር የአካባቢ የደንና የአየር ንብረት ለውጥ ባለስልጣን ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ አብዱ መሀመድ ፕሮጀክቱ የከተማዋን ልማት ከማፋጠን አኳያ የሚኖረው ፋይዳ እጅጉን የጎላ እንደሆነ በመግለጽ የደቻቱ ወንዝ ለድሬዳዋ ትልቅ ሀብት ቢሆኖም በመጥፎ ገጽታ ዕየተነሳ እንደሚገኝ ከተማዋ ከውበት አንጻር ቀድሞ የነበራትን መገለጫ እያጣች እንደምትገኝ ይህን ከግምት ውስጥ በማስገባት ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ፕሮጅክቱ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጅት ለመስራት ያላሰለሰ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ ገልቷል፡፡
    በአስተዳደሩ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ulldp የከተማ የተቀናጀ ተቋማዊ ልማት ፕሮግራም ስድስት ሚሊዮን ብር በሚጠጋ ድጋፍ በሐሮሚያ ዩኒቨርስቲ እየተደረገ የሚገኘው ጥናቱ የአስተዳደሩን ቀጣይ የቀጣይ መቶና ሁለት መቶ አመታት ሁኔታ ትንበያ ላይ የተመሰረተ እንደሆነ በማስተዋወቂያ መድረኩ ተገልጻል፡፡
    በቀረበው የጥናቱ ደረጃ ላይ የውይይት መድረኩ ላይ የተሳተፉት እንደ ተናገሩት ፕሮጀክቱ የድሬዳዋን ገጽታ የሚያጎላ እና ድሬዳዋ ቀድሞ የነበራትን ውበቷ ለመመለስ ከሚሰሩ ስራዎች አንዱና ዋነኛው በመሆኑ ሁሉም የድርሻውን በመወጣት ተፈጻሚነቱን ለማፋጠን እነደሚሰሩ አስተያየታቸውን ገልጸዋል፡፡