በነገው ዕለት በአስተዳደራችን የሚጀመረውን የኢትዮጵያ ቤት ኪንግ ፕሪሚየር ሊግ እና በወቅታዊ ጉዳዮችን ዙሪያ ከመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የተሰጠ መግለጫ፡፡

    በድሬዳዋ አስተዳደር አስተናጋጅነት የሚካሄደው 4ኛ ዙር የቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጫዋታዎች ከነገ መጋቢት 29/2013ዓ/ም ጀምሮ ለ5 ተከታታይ ሳምንታት ይካሄዳል፡፡
    ይህንን እና ሌሎች ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የአስተዳደሩ መንግስት ኮሙዩኒኩሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ እስቅያስ ታፈሰ ለጋዜጠኞች ጋዜጣዊ መግለጫ ሰተዋል፡፡
    በድሬዳዋ አስተናጋጅነት የሚካሄደው የኢትዮጵያ ቤት ኪንግ ፕሪሚየር ሊግ ለማዘጋጀትና ጨዋታን በስኬት እንዲጠናቀቅ አስፈላጊው ዝግጅት መጠናቀቁን የአስተዳደሩ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፉ ተናግረዋል፡፡
    ኃላፉው ከዚህም ጋር አያይዘው ከዝግጅት ምዕራፍ እሰከ አሁን ድረስ የተለያዩ ለውድድሩ ድምቀት የሚሆኑ ሥራዎች የተሰሩ ሲሆን በውድድሩ የሚሳተፉትን ክለቦች እና ቁጥራቸው በርከት ያለ እንግዶች በከተማችን ላይ ይገኛሉ ብለዋል ፡፡
    ይህንን አጋጣሚ ለከተማችን የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞች ይኖረዋል በማለት በተለይም ስፖርት በራሱ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ለጠናከር አንዱ ዘርፍ ከመሆኑም በላይ የብሄር ብሄረሰቦች የሚኖረውን ስፖርታዊ ማስተጋብር የተሻለ ያደረገዋል ብለዋል፡፡
    በተለይም የፋስል ከነማ ደጋፊዎች በድሬዳዋ ጎዳና የቀቡትን አሰፓልት ዳር ቀለምና በጎ ተግባራት አመስግነዋል፡፡
    ድሬዳዋ እንደዚህ ዓይነቶቹን መሰል ውድድሮች በብቃት መስተናገድ የሚትችልበትን አቅም ከመኖሩ በተጨማሪ ከተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች የሚመጡ እንግዶችም የማስተናገድ አቀም እንዳላት የሚመሰክር ነውም ብለዋል፡፡
    የድሬዳዋ ማህበረሰብ የስፖርት ማህበረሰብ ተብሎ የሚገለጽ በመሆኑ የእንግዳ ተቀባይም ነው ይህንን ውድድርም የሚታደሙ እንግዶች በተለመደው የእንግዳ ተቀባይነታቸው እንዲያሰተናግዷቸው ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል ፡፡
    በአሁን ወቅት በአለም አቀፍ እንዲሆም በሀገራችን ሰጋት የሆነውን የኮሮና ቫይረስን ችግር ከምን ጊዜ በላይ ስርጭቱን እየሰፋ ባለበት ሁኔታ ይህንን ከግምት ውስጥ በማስገባት የክለቦቹን ደጋፊዎች በቁጥር ከ10 ደጋፎዎች የማይበልጡ ወደ ውድድር ሜዳውን እንዲገቡ ብቻ ነው የተፈቀደው ሌሎች ያልተፈቀደላቸው ደጋፊዎች መግባት እንደማይቻል ተናግረዋል።
    ውድድሩ የአለም አቀፍ የቲቨ ሽፋን ስለሚያገኝ በቤት ውስጥ መከታተል ይቻላልም ብለዋል፡፡
    የኮሮና ቫይረሰ መከላከል ላይ በህብረተሰቡ ዘንድ ከፍተኛ የሆነ መዘናጋት ያለ ሲሆን በተለይም መንግስት ያወጣውን የጥንቃቄ መመሪያዎችን ህዝቡ እንዲተገበረም በመጠየቅ ይህንን የኮሮና መከላኪያ ጥንቃቄዎችን የማይተገብሩ አካላትም ከሚመለከተው የፀጥታ ተቋማት ጋር በመተባበር አስፈላጊውን እርምጃ ይወሰዳል ብለዋል፡፡
    ኃላፉው ከዚህም በተጨማሪ በሀገራችን የሚካሄደውን 6ኛውን ሀገራዊ ምርጫ እንደ መንግስት አስፈላጊውን ቅደመ ዝግጀት እየተደረገ እንደሚገኘ እና ከቀናት በፊት የመራጮችን ካርድ በመሰጠት ላይ እንዳለ በመጥቀስ ህብረተሰቡ የዚህን ምርጫ ለመሳተፍም ሆን ይሆንለኝ የሚለውን የሚመርጥበትን የመራጪነት ካርድ እንዲወስዱ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡