በድሬደዋ አስተዳደር የምስራቅ ጀግኖች ት/ቤት ተማሪዎች በሀገራቀፍ የመጀመሪያው የሰላም ቀን ባከበሩበት ስነስርዓት ላይ የተገኙት የድሬ ደዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ሙሉካ መሀመድ ባደረጉት ንግግር ለአንድ ሀገር ዘላቂ ሰላምና አብሮነት የታዳጊ ህፃናት የሰላም ዕውቀት ከፊተኛ ሚና ያለው በመሆኑ በየትምህርት ቤቶቹ ተማሪዎቻችን ሰላምና አብሮነትን ፣ መብትና እና ግዴታን በአግባቡ እንዲረዱ ለማድረግ እንዲሁም የተማሪዎችን የሰላም እና የአብሮነት ዕዉቀት ለማጎልበት ተከታታይነት ያለው ስራ የሚሰሩበት መሆኑንና ይህ የዛሬው የሰላም ቀን ይህን ስራ የተጀመረበት በመሆኑ እንካን ለዚህ ቀን በሰላም አደረሳቹ ብላዋል ፡፡
በዚህ የሰላም ቀን ስነስረኣት ላይ አስተያየት የሰጡን ተማሪ ትዝታው ጀጎል እና አብዱረሂም ኢፍታህ ሰላም ሰዎች በአግባቡ ያልተረዱት እጅግ በጣም ጠቃሚ ሀብት በመሆኑ የህን ሀብት ለመጠበቅ “ እኔ የሰላም አንባሳደር ነኝ ” በሚል መሪ ቃል ይህ የሰላምን ጠቀሜታ የማስተማር ስራ ላይ እየሰሩ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
ይህ የሰላም ቀን በዓለማቀፍደረጃ ለ 8ኛ ጊዜ እና በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚከበረውን ስፖርት ለልማትና ለሰላም ቀን ስነስርዓት ላይ የአስተዳደሩ ት/ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሙሉካ መሀመድ እንዲሁም በአስተዳደሩ የብልጽግና ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው በሳቢያን ቁ.2 እና በምስራቅ ጀግኖች ት/ቤቶች በተማሪዎች የሰልፍ ስነ ስርዓት ላይ በመገኘት ዕለቱን ከተማሪዎችና መምህራን ጋር ተከብሮዋል ።


