ያለ ዜጎች ተሳትፎ እውነተኛ ዴሞክራሲና፣ ሕገ መንግስቱን እውን ለማረግ እንደማይቻል ሁሉ ከቅርብ ወራት በኋላ የሚካሄደውን 6ተኛው ሀገራዊ ምርጫ በህዝብ ተሳትፎ የዳበረ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን በእንደዚህ ዓይነቶቹ ስልጠናዎች አማካኝነት ዜጎችን ማስተማር የምርጫው ውጤት ግልጽና በህዝቦች ዘንድ ተቀባይነት ያለው ምርጫ እንዲሆን፡፡
የስልጠናውን ያዘጋጀው ምስራቃዊ የዕድገት ፋና የበጎ አድራጎት ማህበር ከINITIATIVE AFRICA በተገኘው የገንዘብ ድጋፍ 6ተኛው ዙር አገር አቀፍ ምርጫ እና የሥነ-ዜጋ ትምህርት ከአስተዳደሩ የከተማ ቀበሌዎች ከተወጣጡ በበጎ ሥራዎች ላይ ለተሰማሩ ወጣቶች የአሰልጣኞች ስልጠና ሰተዋል፡፡
በስልጠና መክፈቻው ላይ ንግግር ያደረጉት የምስራቃዊ የዕድገት ፋና በጎ አድራጎት ማህበር ዳይሬክተር አቶ ግርማ ቱፋ እንደተናገሩት የዚህ ሥልጠና ዓላማ ሠልጣኞች መራጩ ሕዝብ እና የምርጫ አስፈጻሚዎች ሥነ-ዜጋዊ ዕውቀት፣ክህሎት እና ባህርያት እንዲያዳብሩ እንዲሁም፣ስለ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ እና የዜጎች ተሳትፎ ዕውቀት እንዲኖራቸው የሚያስችል እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
አክሎም አቶ ግርማ ቱፋ ሥልጠናው ለሰልጣኞች ስለ ምርጫ እና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት፣ዕውቀት እና መረጃ ማስጨበጥ ብቻ ሳይሆን፣በዜጎች ዘንድ ለዴሞክራሲያዊ አሠራር እና ስኬት አዎንታዊ አመልካከት እንዲፈጠር የሚያድረግ ነው ብለዋል፡፡
የሀገራችን የምርጫ ስነ-ምግባር መመሪያ ትምህርት ስልጠና ለተሳታፊዎቹ የሰጡት የህግ ምሁር የሆኑት አቶ መብራቱ ገ/ስላሴ የምርጫ ተሳትፎ ዜጎች ተነሳሽነት እንዲኖራቸው እና በምርጫ ሂደት በነቂስ ወጥተው ተሳታፊ እንዲሆኑ፤ በእውቀት ላይ የተመሰረተ ምርጫ እንዲያደርጉ ከፍተኛ የቀስቃሽነት እና አነሳሽነት ሚና ማህበረሰቡ እንዲኖራቸው አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡
ስልጠናው የምርጫ ሕግጋቱን ምንነት መረዳት፣ የምርጫ አስፈፃሚ አካላትን ተግባር እና ሀላፊነት ማወቅ፣ በምርጫ ወቅት ሊነሱ የሚችሉ አለመግባባቶች የሚፈቱበት ሥርዓቶች እና ዜጎች በመራጭነታቸው መወጣት ያለባቸው ሀላፊነቶች እንዲረዱ ለሰልጣኞቹ ትምህርት ተሰቷል፡፡
በመጨረሸም ያነጋገርናቸው የስልጠናው ተካፋዮች በየ አከባቢያቸው ተመልሰው ማህበረሰብ ምርጫ የዜግነት መብት እንደሆነና የሚፈልገውን ሀገር ያስተዳድርልኝ የሚለውን መንግስት የሚመርጥበት ወሳኝ ተግባር መሆኑን ግንዛቤ እንሰጣለን ብለዋል፡፡


