ህዝቡ የኮቪድ 19 ጫና ውስጥ ባለበት ሁኔታ የተማሪዎች የትምህርት ቤት ክፍያ ጭማሪ መደረጉ የህዝቡን ችግር ከግምት ውስጥ ያላስገባ ነው ተባለ ::
በድሬዳዋ አስተዳደር በርካታ የግል፣ የማብረሰብ/የህዝብ እንዲሁም የእምነት ተቋማት ትምህርት ቤቶች በመማር ማስተማር ሂደት ውስጥ በመሳተፍ መንግስት ትምህርትን ለሁሉም ዜጋ ለማዳረስ የሚያደርገውን ጥረት የበኩላቸውን አስተዋጽዎ በማበርከት የተማረ ዜጋ በማፍራት ከፍተኛ እገዛ በማድረግ ላይ ናቸው፡፡ እነዚህ የትምህርት ተቋማት ለተማሪዎች በሚሰጡት የትምህርት አገልግሎትም ከየተማሪው ክፍያ በመቀበል ትምህርትን በማዳረስ ላይ ይገኛሉ፡፡ ከክፍያ ሂደቱ ጋርም ተያይዞ በአስተዳደሩ በተለያዩ በግል፣ በማህበረሰብ/በህዝብና…


