ግንባታዎቹም ለከተማዋ ለነዋሪዎች ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደሚኖረውም ተገልፃል፡፡
መንገድ ለአንድ ሀገር እድገት ብሎም ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ የጎላ ሚና ይኖረዋል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞም በድሬዳዋ አስተዳደር ከ 725 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ እየተገነቡ የሚገኙ አዳዲስ መንገዶችና ነባር መንገዶችን የመጠገን ስራ እንዲሁም ከዚህ ቀደም በከተማዋ ላይ ጎርፍ በሰውና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ከማድረሱ ጋር ተያይዞ ይህንንም ለመከላል ይቻል ዘንድ የጎርፉ መከላከያ ግንባታዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ ፡፡
አሁን ላይ በከተማዋ እየተገነቡ ያሉት የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች በተለይም ከዚህ ቀደም ይስተዋሉ የነበሩ የትራፊክ መጨናነቆችን ከመፍታት ባለፈ ለኢኮኖሚውም መነቃቃት አይነተኛ አስተዋፆ እንደሚኖረው የድሬዳዋ መንገዶች ባለስልጣን ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ደረጄ ፀጋዬ ተናግረው ከድሬዳዋ ጅቡቲ የሚያገናኘው የ 4 ነጥብ 2 ኪሎ ሜትር መንገድ ተገንብቶ ሲጠናቀቅም ለወጪና ገቢ ንግዱ ከፍተኛ አስተዋፆ ከመኖሩም በዘዘለለ በከተማው ያለውን የከባድ መኪናዎች መጨናነቅን በመቀነስ የውስጥ ለውስጥ ኮብልስቶን መንገዶች እንዳይጎዱ ስለሚያደርገው የመንገዱ ግንባታም በአጭር ጊዜ ውስጥ ቢጠናቀቅ ለነዋሪዎች በእጅጉ ጠቀሜታ እንደሚኖረውም ሀላፊው ተናግረዋል፡፡ ሌላው ከተማዋ ለጎርፍ ተጋላጭ ከመሆኗ ጋር ተያይዞ አሁን ላይ እየተገነቡ ያሉት የጎርፍ መከላከያ ግንቦች ህብረተሰቡን ከጎርፍ ስጋት ነፃ እንደሚያደርግም ነው አቶ ደረጄ የተናገሩት፡፡
በከተማው ከፍተኛ በጀት ተይዞላቸው በርካታ መንገዶች ቢሰሩም ነገር ግን የውሀና ፍሳሽ ባለስልጣን እንዲሁም ቴሌ ለስራ በሚል በመንገዶቹ ላይ የተለያዩ ቁፋሮዎች በሚያደርጉበት ወቅት መንገዶቹ እየተጎዱ ሲሆን ይህም ለስራ እንቅፋት እየሆነ ይገኛል ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞም ከፍተኛ የሆነ የቅንጅት ክፍተት እንዳለና ይህንንም ክፍተቶች ማረም እንደሚያስፈልግ የድሬዳዋ መንገዶች ባለስልጣን ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ደረጄ ፀጋዬ ተናግረዋል ፡፡
በድሬዳዋ አስተዳደር እየተነቡ ያሉ አዲስ የመንገድ ፕሮጀክቶች እንዲሁም የነባር መንገዶች ጥገናና የጎርፍ መከላከያ ግንባታዎች መካሄዳቸው ለከተማዋ ነዋሪዎች በእጅጉ አስፈላጊ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ እየተሰሩ ባሉት ስራዎች ደስተኛ መሆናቸውን የከተማዋ ነዋሪዎች ተናግረው ነገር ግን ግንባታዎቹ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተገንብተው መጠናቀቅ እንዳለባቸውም ነው ነዋሪዎቹ የተናገሩት፡፡


