በድሬዳዋ አስተዳደር በ 350 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ለሚገነባው የብረታ ብረትና ሲሚንቶ ማምረቻ ኢንዱስትሪ የመሰረት ድንጋይ በዛሬው እለት ተቀመጠ ።
በድሬዳዋ አስተዳደር ከመልካ ጀብዱ ወጣ ብሎ በኢንዱስትሪ ፓርክ አቅራቢያ በ 103 ሄክታር መሬት ላይ በኢስት አፍሪካ ሆልዲንግና በዌስት ኢንተርናሽናል ሆልዲንግ ኩባንያዎች በሽርክና ለሚገነባው የኢንዱስትሪ ኮምፕሌክስም የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አደም ፋራህን ጨምሮ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አህመድ መሀመድ ቡህ ፣ የሱማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፌ መሐመድ እና ምክትላቸው አቶ ኢብራሂም ኡስማን፣ የንግድ…


