በድሬዳዋ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽን ሜዳ በብልጽግና ፓርቲ አዘጋጅነት የከተማውን ወጣቶች ያሳተፈ የቁንጅና ውድድር ተካሄደ::

    የቁንጅና ውድድሩ የብልጽግና ፓርቲ የቅስቀሳ ስራ አካል ሲሆን በውድድሩ ተሳታፊ የሆኑ ወጣቶች የብልጽግና ፓርቲ በቀጣይ አምስት አመት ሊሰራቸው ያሰባቸውን እቅዶች በተመለከተ ወጣቶች በተረዱት አግባብ የፈጠራ ክህሎታቸውን ተጠቅመው ጥበባዊ ውበትን በተላበሰ መልኩ ለታዳሚ አቅርበዋል፡፡ በውድድሩ ተሳታፊ የሆኑት ወጣቶች በተላያዩ ክበባት ተሳታፊ የሆኑና በፍቃደኝነት በውድድሩ ተሳታፊ ለመሆን የፈቀዱ ወጣቶች በውድድሩ መሳተፋቸውን የድሬደዋ ብልጽግና ፓርቲ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መመሪያ ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ረሂማ አወል ገልጸውልናል፡፡ በመድረኩ ላይ ከ300 በላይ ታዳሚዎች የተሳተፉ ሲሆን በውድድሩም 13 ሴትና 6 ወንድ ሞዴሎች ተካፋይ መሆናቸውን ወ/ሮ ረሂማ ተናግረዋል፡፡ ሞዴሎቹ በቃረቡት ስራም በዳኞች ተገምግሞ አሸናፊዎች ተለይተዋል፡፡ በዚህም መሰረት
    ከሴት ተወዳዳሪዎች
    1ኛ– ሞዴል ሰሎሜ ወንድይፍራው
    2ኛ– ሞዴል ርብቃ ሰለሞን
    3ኛ– ሞዴል ቤተል አሰፋ
    ከወንድ ተወዳዳሪዎች መሀልም
    1ኛ– ሞዴል ንፍታሌም ለማ
    2ኛ–ሞዴል ናትናኤል ንጉሴ
    3ኛ–ሞዴል ስንታየው አበራ
    ውድድራቸውን አጠናቀዋል፡፡