የብልፅግና ፓርቲ የዘመድ ጥየቃና የመደጋገፍፍ ስነ_ስርዓት በቀበሌ 08 አካሄደ።

    ድሬደዋ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት አዘጋጅነት በህጅራ አቆጣጠር 1442 ታላቁ የረመዳን ፆምን ምክኒያት በማድረግ የዘመድ ጥየቃ እና አቅመ ደካማዎችን የመጠየቅ የዝምድና ማጠናከር ስነ_ስርዓት በቀበሌ 08 በተለምዶ ለገሀሬ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ተካሄዷል።
    በዝግጅቱ ላይ በድሬደዋ የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ፕሬዝዳት ወ/ሮ ሁክሚያ መሀመድ ጨምሮ የሊጉ አባላትና የፓርቲ አመራሮች የተሳተፉ ሲሆን በቀሌዉ የብልፅግና ፓርቲን ወክለዉ የተለያዩ ሀይማኖት ተከታዬች አቅመ ደካሞችን የድጋፍና የዝምድና ጥየቃ ስነ_ስርዓት አካሄደዋል።
    በዝግጅቱ ላይ በድሬደዋ የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ፕሬዝዳት ወ/ሮ ሁክሚያ የተለያዩ ሀይማኖት ተከታይ የፓርቲው አባላት የዝምድ ማጠናከር ባለን የመደጋገፍ እና አብሮነትን ለማጓልበት ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን እና በቀጣይም መሰል ስነ_ስርዓቱ የሚቀጥል መሆኑን አብራርተዋል።
    በዝግጅቱ ላይ የሴቶች እና ህፃናት ቢሮ ሀላፈ ወ/ሮ ከሪማ አሊ ጨምሮ የተለያዩ የአስተዳደሩ እና የድሪጅት አመራሮች ተሳትፈዋል።