አራቱ የገጠር ፖሊስ ጣቢያዎች በድጋፍ የተበረከተላቸውን ዘይት ፤ፓስታ እና ሩዝ ተረከቡ ፡፡

    በዛሬው እለት በአራቱም ገጠር ፖሊስ ጣቢያዎች ተገኝተው የምግብ ሸቀጣሸቀጦቹን ያስረከቡት የድሬዳዋ አስተዳዳር ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ እና የሰው ሀብት ልማት ዘርፍ ሃላፊ ም/ኮሚሽነር ውቢት በፍቃዱ ናቸው፡፡
    የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ የምግብ ሸቀጦቹን ለፖሊስ አባላቱ ባስረከቡበት ወቅት እንደተናገሩት ፖሊስ የህዝቡን ሰላም እና ደህንነት ማረጋገጥ ከቻለ የህዝብን አመኔታ መፍጠር ይችላል ብለዋል፡፡
    በድሬዳዋ አስተዳደር ዙሪያ የሚገኙ የገጠር ፖሊስ ጣቢያዎች የአካባቢያቸውን ሰላም ለማረጋገጥ ቀን ከሌት መስራት ይገባቸዋል ያሉት ኮሚሽነር ዓለሙ ለገጠር ፖሊስ ጣቢያዎች የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡
    ድጋፉ የተደረገላቸው ቢዮአዋሌ፤ዋሂል፤ቃልቻ እና ጀልዴሳ ፖሊስ ጣቢያዎች ሲሆኑ በአራቱም ገጠር ፖሊስ ጣቢያ የሚገኙ አመራር እና አባላት በተደረገላቸው ድጋፍ መደሰታቸውን ተናግረዋል፡፡
    ከዚህ ቀደም ለገጠር ፖሊስ ጣቢያዎች የሚደረግ ድጋፍ አልነበረም ያሉት አባላቱ ከለውጡ ወዲህ የድሬዳዋ ፖሊስ ለገጠር ፖሊስ ጣቢያዎች ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን አድንቀዋል፡፡
    ቀደም ሲል እነዚህን የዋጋ ግምታቸው ከአንድ መቶ ሺብር በላይ የሚሆኑ ሀምሳ ኪስ ሩዝ፤ሀምሳ ደርዘን ፓስታ እና ሀምሳ ፍሬ የምግብ ዘይት ፤በገጠር ፖሊስ ጣቢያ በግዳጅ ላይ ለሚገኙ አባላት አዲል ጠቅላላ አስመጪ ድጋፉ ማድረጉን መዘገባችን ይታወሳል።
    ምንጭ፦ድሬ ፖሊስ