በቀበሌ 09 ታላቁን የረመዳን ፆም ምክንያት በማድረግ የአፍጥርና ድጋፍ የማድረግ ፕሮግራም ተካሄዷል ።
1442 ኛውን ታላቁን የረመዳን ፆምን ምክንያት በማድረግ በድሬዳዋ ብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ አዘጋጅነት በከተማችን በሚገኙ የተለያዩ ቀበሌዎች በጋራ ከማፍጠር ባለፈ አቅመ ደካማ ለሆኑ ነዋሪዎች ድጋፍ ሲደረግ ቆይቷል። በትናንትናው እለትም በ 09 ቀበሌ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አህመድ መሀመድ ቡህን ጨምሮ ከፍተኛ የአስተዳደሩ አመራሮች ፣ የድሬዳዋ ብልፅግና ፓርቲ አመራሮች ፣ የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም የእምነቱ ተከታዮች በተገኙበት በከተማ ደረጃ የመጨረሻ የሆነው በጋራ የማፍጠርና አቅመ ደካማ ለሆኑ ወገኖች ድጋፍ የማድረግ ስነ-ስርዓት ተካሂዷል ።
በስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አህመድ መሀመድ ቡህ በታላቁ የረመዳን ፆም ወቅት በጋራ ከማፍጠር በዘለለ ከተማችን ድሬዳዋ የምትታወቅበትን በጋራ በአንድነት ተቻችሎ የመኖርና የመረዳዳት ባህላችንን ማዳብር እንደሚገባ ተናግረው ከታላቁ የረመዳን ፆም ባለፈ በቀጣይም መሰል የመረዳዳት ባህሎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባም ነው አቶ አህመድ መሀመድ ቡህ በእለቱ ያስታወቁት ።
ባለፍት ቀናት የረመዳን ፆምን ምክንያት በማድረግ በከተማችን በሚገኙ ቀበሌዎች ሲካሄዱ የነበሩት በጋራ የማፍጠርና ድጋፍ የማድረጉ ተግባር እንዲሳካ ከፍተኛ አስተዋፆ ለነበራቸው የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ፣ የብልፅግና ፓርቲ አመራሮችና እጩዎች ፣ የቀበሌ አመራሮች እንዲሁም የከተማዋ ነዋሪዎች በድሬዳዋ ብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ስም ምስጋናቸውን የድሬዳዋ ብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ሀላፊ የሆኑት ወ/ሮ ሁክሚያ መሀመድ አቅርበዋል ።
በ 09 ቀበሌ በተካሄደው የአፍጢርና የድጋፍ ፕሮግራም ላይ የተገኙት የቀበሌው ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ ሀሰን ኢጌ እንዲሁም በትራንስፖርት ባለስልጣን ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሮ ሰአዳ አዋሌ የከተማው ነዋሪዎች ለ 6 ተኛው ሀገራዊ ምርጫ የሚሆን የመራጮች ካርድ በመውሰድ ዘር ፣ ብሄር ፣ ሀይማኖት ሳይል ሁሉንም አቃፊ የሆነውን ብልፅግና ፓርቲን ሊመርጡ እንደሚገባም ተናግረዋል ።


