በቀጣይ ዕሮብና ሐሙስ በአስተዳደሩ ይጥላል ተብሎ ለሚጠበቀው ከባድ ዝናብ ህብረተሰቡ ቅድመ ጥንቃቄ እንዲያደርግ የግንዛቤ ማስጨበጫ ተሰጠ።

    ድሬዳዋ ላይ በተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት ጉዳት እየተከሰተ እንደሚገኝ የድሬዳዋ ህብረተሰብ ልማት ኤጀንሲ ዳይሬክተር አቶ ጎንፋ ሞሲሳ ጠቁሙዋው፡፡ አሁን በቀጣይ በድሬዳዋ ዕሮብ እና ሐሙስ በሚጥለው ዝናብ ለሚደርሱ አደጋዎች ህብረተሰቡ አውቆና ግንዛቤ ወስዶ እራሱን እንዲጠብቅ አስታወቀዋል፡፡ እዲሁም አደጋዎችን ለመቀነስ የግንዛቤ ማስጨበጫ በዘጠኙም የድሬዳዋ ቀበሌዎች በሚገኙ 122 መንደሮች ለሚኖሩ ማህበረሰቦች በተጠሪዎቻቸው አማካኝነ ግንዛቤ እየተሰጠ እንደሚገኝ አቶ ጎንፋ አያይዘው ተናግረዋል፡፡ እየተሠራ ያለው የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ ብቻ ሳይሆን እንዲያወያዩና ቅስቀሳ እንዲያደርጉ ጭምር እየተደረገ እንደሚገኝ አክለው ጠቁመዋል፡፡
    ይህም የሚመለከታቸው አካላቶች ከመንገዶች ባለስልጣን እንዲሁም አደጋ መከላከልና ስጋት ጋር በመሆን አደጋዎች ምንድን ናቸው? ለመከላከል እና ከአደጋ እንዴት መውጣት ይቻላል? ለሚለውን ጥያቄ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ መሰጠቱን ተናግረዋል፡፡ ህብረተሰቡም በቀጣይ በመንገዶች ባለስልጣን በኩል የተገዙ ማዳበሪያዎች አሉ፡፡ ይህንንም ሙሉ በሙሉ ለሁሉም ለማድረግ አቅም ስለማይፈቅድ ለጎርፍ ተጋላጭ ለሆኑ አካባቢዎች የሚሆን ማዳበሪያ አፈር ተሞልቶ በየደጃፋቸው እንዲያደርጉት በተጠሪዎቻቸው አማካኝነት እንደሚከፋፈልም ጠቁመዋል፡፡ ህብረተሰቡም አብሮ የመኖር እሴቱን በዚህ የተፈጥሮ አደጋ ወቅት በመተባበርና በመደጋገፍ እንዲያሳልፍ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
    በአሁን ሰዓት በከተማችንም በገጠርም ከባድ ዝንብ እየጣለ እንደሚገኝ የድሬዳዋ የመንገዶች ባለስልጣን ስራ አስኪያጅ ደረጀ ጸጋዬ ተናግረዋል፡፡ ይህንንም ከብሔራዊ ሜትሮሎጂ ድርጅት ከድሬዳዋ አደጋ ስፈጋት ቅነሳ ጽ/ቤት በኩል ቅድመ ማስጠንቀቂያ መነገሩን አቶ ደረጀ ጸጋዬ ገልፀዋል፡፡ አያይዘውም የፊታችን ዕሮብ እና ሀሙስ መጠኑ ከፍ ያለ ዝናብ በአስተዳደሩ ሊከሰት ስለሚችል ማህበረሰቡም ይህንን አውቆ አካባቢውንም እራሱንም ከዚህ አደጋ መጠበቅ እንደሚገባው ጠቁመዋል፡፡
    ህብረተሰቡ በአካባቢያቸው ያሉ የጎርፍ ቦዮችን በመክፈትና የጎርፍ ስጋት ላለባቸውን አካባቢዎች ወደ 3,000 የሚሆኑ ማዳበሪያዎች ተገዝተው በጊዜያዊ መፍትሄነት ህብረተሰቡ አፈር ሞልቶ በየደጃፉ እንዲያደርገው የማንቃት እና የማስተባበር ስራዎች መሰራታቸውን ጠቁመዋል፡፡ ሰሞኑን በደረሰው አደጋ ለተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎች የቀብር ማስፈጽም እና የጊዜያዊ መጠለያ መውሰድ ስራዎች መሰራታቸውን አቶ ደረጀ ጠቅሰው ከሀዘናቸው ሲመለሱም መልሶ የማቋቋም ሥራዎች እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡