የመንገድ ላይ የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ የአሽከርካሪውና የማህበረሰቡ ድጋፍ ሊጠናከር እንደሚገባ ተገለፀ፡፡

    በዘንድሮው የበጀት አመት በተወሰደ ቅንጅታዊ የቁጥጥር ስራ የተሻለ ውጤት መገኘቱን በፖሊስ ኮሚሽን የመንገድ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት አስታውቋል፡፡
    የዳይሬክቶሬቱ ዳይሬክተር ኢኒስፔክተር ይሄነው ሽፈራው እንዳስታወቁት በከተማችን ድሬደዋ ከጊዜ ጊዜ እየደረሰ የሚገኘውን የትራፊክ አደጋ መንስኤ በመለየት በተሰራ የቁጥጥር ስራ አደጋን በመቀነስ የመንገድ ፍሰቱት ለማሳለጥ ተችሏልም ብለዋል፡፡
    ሌላው ከዚህ በፊት መጠነኛ አደጋዎች ሲከሰቱ አሽከርካሪዎች እርስ በእርስ በሚያደርጉት ስምምነት የትራፊክ ፖሊስ በስፍራው ሳይገኝ አደጋው ሳይመዘገብ ይታለፍ እንደነበር አስታውሰው ይህ ደግሞ በከተማዋ የሚደርሰውን ትክክለኛ የአደጋ መጠን ለማወቅ አዳጋች ነበር ብለዋል፡፡
    ዘንድሮ ይህን በመቅረፍ ሁሉንም አደጋዎች በመዝገብ እንዲመዘገቡ መደረጉንና ይህም በተለይ የሚደርሱ አደጋዎችን ለይቶ የቁጥጥር ስራን ለማጠናከር እገዛው የጎላ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
    ሌላው ማንኛውም አሽከርካሪ ሰሌዳን ፈቶ ለማምለጥ ሲሞክር ከተያዘ እስከ 5ሺ ብር በሚደርስ መቀጮና መንጃ ፍቃዱን ሙሉ ለሙሉ እስከመሰረዝ ለሚደርስ ቅጣት እንደሚዳረግ ተናግረዋል፡፡
    በተመሳይም ሰሌዳን ለእይታ ምቹ ባልሆነ ቦታ ማሰር እንዳይታይ ጭቃ መቀባትና ተያያዥ ተግባራት በተመሳሳይ በ4ሺ ብር መቀጮና መንጃ ፍቃድን እስከመሰረዝ ለሚደርስ ቅጣት ስለሚዳረጉ አሽከርካሪዎች ከመሰል ህገወጥ ተግባራት እንዲቆጠቡ አሳስበዋል፡፡
    በሌላ በኩል የሞት አደጋ ያስከተለ ለአንድ አመት እንዲሁም ከባድ አደጋ ያደረሰ ለ6ወር መንጃ ፍቃዱ ይታገዳል በመሆኑም አሽከርካሪዎች ተጠንቅቀው በማሽከርከር ራሳቸውን ከቅታት ማህበረሰቡን ከአደጋ ይታደጉ ብለዋል፡፡
    በስተመጨረሻም ያለአግባብ ታሪፍ መጨመር ከማህበረሰቡ በሚደርስ ጥቆማ መሰረት ከ500-1ሺ በር ያስቀጣልም ነው ያሉት፡፡
    ምንጭ፦Federal Transport Authority Dire Dawa Branch