“ኢትዮጵያን ለማዳን የቱንም ርቀት እንጓዛለን፤ የቱንም መስዋዕትነት እንከፍላለን!” በሚል መሪ ቃል ኢትዮጵያን የማዳን ዘመቻ የድጋፍ እግር ጉዞ በድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ተካሄደ
በእግር ጉዞው ላይ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ነዋሪዎች ፣ ምክትል ከንቲባ አህመድ መሐመድ ቡህ እና የካቢኔ አባላት ተሳትፈዋል፡፡
የድሬዳዋ ከተማ ህዝብና የመንግስት ሠራተኛው ለአገር መከላከያ ሠራዊት ያለውን አጋርነት እና ድጋፍ የሚያጠናክርበት ይህ ኢትዮጵያን የማዳን ዘመቻ የድጋፍ እግር ጉዞ ላይ “ክብርና ሞገስ ህይወቱን ለሰጠን መከላከያ ሰራዊት!” ፣ ኢትዮጵያን ለማዳን እዘምታለሁ የትም ፣ መቼም በምንም!” የሚሉና ሌሎች መልዕክቶች ተላልፈዋል።
የጤና ባለሞያዎች የመንግስት ሰራተኞች ወጣቶችእንዲሁም በተለያየ ሞያ ዘርፍ የተሰማሩ የአስተዳሩ ነዋሪዎችም ሀገራቸዉ የጣለችባቸውን ሀላፊነት በታማኝነትና በቅንነት ለማገልገል ቃል ገብተዋል ።
በተጨማሪም ኢትዮጵያዊነት በዘመናት መካከል ደምቆ የሚታይ በአለት ላይ የተመሰረተ ፅኑ ማንነት ነው የሚሉ መሠረታዊ ሃሳቦች አንግበው ድጋፋቸውን ገልፀዋል፡፡
ሠራተኞቹ ኢትዮጵያን ለማዳን የቱንም ርቀት እንጓዛለን ፤የቱንም መስዋዕትነት እንከፍላለን ፤ክብርና መጎስ ህይወቱን ለሰጠን መከላከያ ሰራዊት፤ኢትዮጵያን ለማዳን እዘምታለሁ፣የትም-መቼም-በምንም የሚሉ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል ።
ለአገር ልዕልናና ህልውና መረጋገጥ ህይወቱን እየሰዋ ለሚገኘው የመከላከያ ሰራዊትና እና ልዩ ኃይሎች የእግር ተጓዦቹ የደም መለገስ ፕሮግራም ተካሂዷል
በሰልፉ ላይ የተሳተፉ ነዋሪዎች በተለይም ወጣቶች ከደም ልገሳ ባሻገር ከአገር መከላከያና የጸጥታ መዋቅሩ ጎን በመሰለፍ አገርን ለማዳን ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል ።
በስነ-ስርዓቱ ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች፣ ሰርከስ ድሬዳዋ እና የድሬዳዋ ማርሽ ባንድ ቀስቃሽና ድጋፉን የሚያጠናክር ዝግጅት ቀርቧል፡፡


