ለምስራቅ ዕዝ ደረጃ ሶስት ሪፈራል ሆስፒታል 300 ፍራሽና እና 300 አንሶላ ድጋፍ ተደረገ ።

    በድሬዳዋ አስተዳደር በሚገኙ የተለያዩ ቀበሌዎች እንዲሁም አስተዳደሩ ለጀግናው መከላከያ ሰራዊትና ለልዩ ሀይል አባላት የሚሆኑ የተለያዩ ድጋፎች እየተደረጉ ይገኛሉ ። ከዚሁ ጋር ተያይዞም በዛሬው እለት በድሬዳዋ አስተዳደር የተቋቋመው የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ በድሬዳዋ ለሚገኘው የምስራቅ ዕዝ ደረጃ ሶስት ሪፈራል ሆስፒታል 300 አንሶላ እና 300 ፍራሽ ድጋፍ አበርክተዋል::
    በዚሁም የድጋፍ ስነ-ስርአት ላይ የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የንግድ ኢንደስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሀላፊ የሆኑት አቶ ከድር ጁሀር ለሀገር መከላከያ ሰራዊት በድሬዳዋ የሚገኙ የተለያዩ ባለሀብቶችን በከተማም ሆነ በገጠር የሚገኙ ነዋሪዎች ድጋፋቸውን በማድረግ ላይ እንደሚገኙ ተናግሮ የድሬዳዋ አስተዳደርና የከተማው ነዋሪዎች የምስራቅ ዕዝ ደረጃ ሶስት ሪፈራል ሆስፒታል እንዲሁም የመከላከያ ሰራዊት አባላትን ድጋፍ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆናቸውንም ነው አቶ ከድር ጁሀር የተናገሩት ።
    የህግ ማስከበር ግዳጅ ከተጀመረ ጊዜ አንስቶ የድሬዳዋ አስተዳደር ከጎናቸው እንደነበር የምስራቅ እዝ ደረጃ ሶስት ሪፈራል ሆስፒታል አዛዥ የሆኑት ኮረኔል ብርሀኑ ዘውዴ ተናግረው ለዚህም ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።