ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ፍታዊ በሆነ አገልግሎትና አሰጣጥ ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ እየሰራ እንደሚገኝ የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ አሳወቀ።
ይህ የተገለፀው የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ በስሩ ካሉ የጤና ተቋማት ጋር የ2013 በጀት አመት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ ላይ ሲሆን ለሁለት ተከታታይ ቀናት በሐረማያ ዪኒቨርስቲ በተካሄደው የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ለምለም በዛብህ እንደ ተናገሩት በ2013 በጀት አመት የእናቶችና የጨቅላ ህፃናት ሞት፣ ተላላፊ የሆኑ በሽታዋችንና ኤች አይ…


